+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል የክፍያ ስርዓት በጋር አብሮ ለመስራት በሚያስችሏቸው ጉዳዮች ላይ ስምምነት ተፈራረሙ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢ-ሰርቪስ ተጠቃሚ የሆኑት የመንግስት ተቋማት የ ሲ ቢ ኢ ብር የክፍያ ስርዓት እንዲጠቀሙ እና የአገልግሎት ክፍያዎቻቸው በሲ ቢ ኢ ብር እንዲቀበሉ የሚያደርግ ስምምነት ፈጽመዋል፡፡
በስምምነት ስነ ስርዓቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ እነዚህን የመንግስት አገልግሎቶች ከዲጂታል የክፍያ ስርዓት በማስተሳሰር ለተገልጋዩ ህብረተሰብ የክፍያ ሰርዓቱን ቀላል እና ምቹ የሚያደርግና አገልግሎት ለሚያቀርቡ የመንግስት ተቋማትም የክፍያ አሰባሰብ በማዘመን ቀላል ማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡
በ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ መሰረት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ2500 በላይ የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታይዝድ እንዲሆኑ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው እስካሁን ከ800 በላይ የመንግስት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ የተደረጉ ሲሆን በሚኒስቴር መስሪያቤቱ የለማውን የኢ-ሰርቪስ ፕላትፎርምን በመጠቀም 26 የመንግስት ተቋማት አገልግሎታቸውን ዲጂታላይዝ በማድረግ ለህብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ ዱቪዥን ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ወጋየሁ ገብረማርያም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ክፍያ አማራጮችን በተለያዩ ጊዜያት ለደንበኞቹ አስቀድሞ በማቅረብ የሚታወቅ ሲሆን ኢ-ሰርቪስ ፕላትፎርም ላይ አገልግሎት የሚያቀርቡ የመንግስት ተቋማት የአገልግሎት ክፍያቸውን ሲ.ቢ.ኢ ብርን ሲጠቀሙ ቀልጣፋና ቀላል አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች