+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ፋሲሊቲ ላይ በጋራ ለመስራት መከሩ።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ የተመራው ቡድን በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ፋሲሊቲ ላይ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በመጎብኘት በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

ጉብኝቱ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዲጂታል ሲስተም እንዲኖር በዘርፉ ላይ ትኩረት አድርገው ከሚሰሩ ተቋማት ጋር በትብብር በመስራት የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማጎልበት ያለመ ነው።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ በአለም አቀፍ ከፍተኛ እውቅና ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ፋሲሊቲ በቴክኖሎጂና በዲጂታል ለማዘመንና ጊዜውን የዋጀ እንዲሆን በትብብር መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

ተቋሙ አዲስ አበባን የአፍሪካ እና ከዚያም በላይ ድንበር ተሻጋሪ የኢ-ኮሜርስ ሎጂስቲክስ ማዕከል እንድትሆን ክፍተቶችን መቅረፍ በሚያስችለው የዲጂታል ዘርፉ ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል።

ሀገራችን ዲጂታል ኢትዮጵያን 2025 እውን ለማድረግ ሰፊ ስራዎችን ሰርታለች ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው የሀገራችን የኢኮኖሚ እድገት ፈጣን ውጤት እንዲያስመዘግብ የቴክኖሎጂና የዲጂታል ዘርፉ ላይ የሚሰሩ ስራዎች ከመቼውም በላይ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለበቸው ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢ-ኮሜርስ ሎጀስቲክ አገልግሎት ማናጀር አቶ ቴዎድሮስ አያሌው ኢትዮጵያ የሀገራዊ ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የውጪ እቃ ንግዱን ዘመናዊ አሰራርን በማምጣት በዓለም ዓቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ በመሆን ተጨማሪ የገበያና የስራ እድል መፍጠር ይቻላል ብለዋል።

በተደረገው ውይይት የተጀመሩ መልካም ስራዎች ሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ላይ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጡ የትብብር ስራው ወሳኝ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ