+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሙያ ማህበራት ሕብረት ጋር በጋራ ለመሥራት መከረ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የሙያ ማህበራት ሕብረት ጋር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በፈጠራ መስኮች ዙሪያ የጋራ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ጥምረት ከፈጠሩ የሙያ ማህበራት ጋር ሁሉን አካታች የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን የሕብረተሰቡን ችግር ፈቺ የሆኑ የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ ተግባር ለመለወጥ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ የምክክር መድረክ በዘርፉ ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን በአግባቡ ለመጠቀምና ብሔራዊ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፖሊሲን በብቃት ለመደገፍ የሚያስችል መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አስረድተዋል።
የሀገራዊ የምርምር ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ በበኩላቸው፣ ሚኒስቴሩ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዙሪያ በትብብር ለመስራት ከሙያ ማህበራቱ ጋር በመተሳሰር ተግባራዊ ምርምሮችን ለማከናወን ማቀዱን ገልጸዋል።
መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው የሙያ ዘርፎች ተደራጅተው የመጡ ማህበራትን በማገዝ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሕብረተሰቡን ችግር በምርምር ለመፍታት በትኩረት እንደሚሠራ ሥራ አስፈፃሚው አብራርተዋል።
የሕብረቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዓለማየሁ መኮንን ሕብረቱ ከሁሉም የሙያ መስኮች የተውጣጣ አካታች ስብስብ መሆኑንና የራሱን ራዕይና ስትራቴጂ ቀርጾ ሕጋዊ ሰውነት ኖሮት ለሀገራዊ ልማት አስተዋጽኦ ለማበርከት እንዲሁም እንደ ሀገር የሙያና የሙያተኛ ክብር የሚጠበቅበት ሥርዓት እንዲሰፍን እየሠራ መሆኑን ፕሬዚዳንቱ አስታውቀዋል።
በመጨረሻም ከማህበራቱ ጋር የሚሰሩ ሀገራዊ ስራዎችን ለማጎልበት የሚሰሩ ስራዎችን ለማጠናከር ቀጣይነት ያለው ግንኝነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጋራ ተደርጓል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች