+251111265737

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከዓለም ባንክ ጋር ስትራቴጂካዊ ውይይት አካሄደ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክብርት ፍሬሕይወት ታምሩ በዲቪዥን ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ከተመራው የዓለም ባንክ ልዑካን ቡድን ጋር በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች እና አጋርነታቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ውይይቱ በሦስት ዐበይት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ሲሆን፤ እነዚህም የኢትዮጵያ ዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት መጠናቀቅ፣ የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የዲጂታል ትስስር ፕሮጀክትን (EARDIP) ከኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ቀዳሚ አጀንዳዎች ጋር ይበልጥ ለማቀናጀት መገምገምና አስፈላጊውን ማሻሻያ ማድረግ፣ እንዲሁም በሚኒስቴሩ የአምስት ዓመት የዘርፍ ስትራቴጂ ማዕቀፍ መሠረት የወደፊት የትብብር ሥራዎችን ማጠናከር ናቸው።

ሚኒስቴሩ እና የዓለም ባንክ የዲጂታል ፋውንዴሽን ፕሮጀክት መጠናቀቅን አስመልክቶ ውይይታቸውን ለመቀጠል እንዲሁም ለቀጣይ ሥራዎች ግብዓት የሚሆኑ መልካም ተሞክሮዎችን ለመቀመር ተስማምተዋል። በተጨማሪም የዓለም ባንክ ልዑካን ቡድን የምሥራቅ አፍሪካ ቀጠናዊ የዲጂታል ትስስር ፕሮጀክት (EARDIP) ተግባራትን ከሚኒስቴሩ ጋር በጋራ ለመገምገምና የፕሮጀክቱን ድንበር ተሻጋሪ ዓላማዎች እያሳኩ የትግበራውን ሂደት ይበልጥ ለማሳለጥ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያዎችን ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል።

​ክብርት ሚኒስትሯ ባንኩ በጋራ ለመሥራት ያሳየውን ዝግጁነት በደስታ ተቀብለዋል። ሚኒስቴር መ/ቤቱ የአምስት ዓመት የዘርፍ ስትራቴጂውን ከታላቁ የመደመር ስትራቴጂ ጋር በተጣጣመ መልኩ በማዘጋጀት ላይ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የወደፊት ትብብሩ የሕዝብ አገልግሎቶችን ማሻሻል፣ በሁሉም ዘርፎች ዕድገትን መደገፍ እና የሥራ ዕድሎችን ማስፋት በሚችልበት ሁኔታ ላይ በትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።

​ሚኒስቴር መ/ቤቱ የዓለም ባንክ ለረጅም ጊዜ ላደረገው የልማት አጋርነት እና ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላበረከተው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ምስጋናውን አቅርቧል።

Ministry of Finance - Ethiopia

World Bank Group

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251111265737
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2026 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ