+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጃፓን ዓለም ዓቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ጋር በኢትዮጵያ የስታርታፖች ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጃፓን ዓለም ዓቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ጋር በኢትዮጵያ የስታርታፖች ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ ለመስራት በሚያስችል ፕሮጀክት ዝርዝር ዕቅድ ላይ በመምከር የስምምነት ሰነድ ፈርመዋል።

የተደረገው የስምምነት ፕሮጀክት በቀጣይ ሦስት ዓመታት የሚተገበር ሲሆን፤ የስታርታፕ ልማት ስርዓት ከአለም አቀፉ ጋር የማስተሳር ስትራቴጂን ማዘጋጀት፣ ስታርታፖችን ማፍራትና በዓለም አቀፍ ሀገራት ቢዝነሳቸውን በማስፋት ከኢንቨስተሮች ጋር በጋራ መስራት እንዲችሉ ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ስታርታፖች አዳዲስ ምርቶችን በማውጣት፣ አገልግሎትን በማዘመን አዳዲስ ስራዎችንና ሃብትን በመፍጠር የኢኮኖሚ ዕድገቱ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽዖ የሚያደርጉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ስታርታፖች በእድገት ጉዟቸው ላይ በርካታ መሰናክሎችና ፈተናዎች ስለሚገጥማቸው ልዩ ክትትልና ድጋፍ ለማድረግና ስነምህዳሩ የተሳለጠ እንዲሆነ የተደረገው ስምምንት ጉልህ ሚና እንደሚኖረው አንስተዋል።

የጃፓን ዓለም ዓቀፍ የትብብር ኤጀንሲ ተወካይ አቶ ሳቶሜ ጁን/Mr. Satome Jun የስታርታፖች ስነ-ምህዳር የማጎልበት ፕሮጀክቱን የጃፓን መንግስት በኬኒያ፣ በታንዛኒያ እና በኢትዮጵያ ለማከናወን የሰው ኃይል እና በጀት በመመደብ በቅርቡ ትግበራውን እንደሚጀም ገልጸዋል።

የጃፓን መንግስት በ JICA በኩል ለኢትዮጵያ ስታርታፖች ዕድገት እና መስፋፋት በርካታ ድጋፎችን እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው የተደረገው ስምምነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እንደሚያደርገው ተጠቁሟል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ