+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች 19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል አከበሩ።

19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ቀን በዓል ሀገራዊ መግባባት ለህብረብሔራዊ አንድነት በሚል መሪ ቃል በሚኒስቴሩ የተከበረ ሲሆን ‹‹ኅብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ ተግዳሮቶቹ እና የመፍትሄ ሀሳቦቹ ››የሚል የመወያያ ጹሁፍ ላይም የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ውይይት አድርገዋል።

በዝግጅቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ሀገራዊ አንድነታችንን በማጠናከር ያሉን እምቅ ሀብቶች መጠቀምና ሀገራችን የጀመረችውን የኢኮኖሚ ጉዞ ማፋጠን ይጠበቅብናል ብለዋል።

አያይዘውም በዓሉን ስናከብር በውስጣችን የሚፈጠሩት ሀገራዊ አለመግባባቶች ለመፍተታት የተጀመረውን ስራ ለማገዝ በሀሳብ የበላይነት ማመን እና አንድነታችን ማጠንከር አለብን ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ሀገራዊ መግባባት ሲኖር የጠነከረች እና ህብረብሔራዊ አንድነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያ እንድትኖረን ያደርጋል ብለዋል።

እንደሚኒስቴር መስርያ ቤት የስታርአፕ፣የምርምርና ኢኖቬሽን፣የቴክኖሎጂ ሽግግርና ኢንዱስትሪያላይዜሽን ስራዎችን በመደገፍና በማጠናከር ዘርፉ በሀገር ኢኮኖሚ የሚኖረውን ፋይዳ ማሳደግ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

በበዓሉ ፕሮግራም ላይ በሚኒስቴሩ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ "ኅብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ፣ ተግዳሮቶቹ እና የመፍትሄ ሀሳቦቹ" የሚል የመዋያያ ሰነድ በማቅረብ ውይት የተካሄደ ሲሆን እንደሀገር የተሰጠንን የቴክኖሎጂና ዲጂታላይዜሽን ጉዞ ከግብ በማድረስ መላው ትዮጵያዊያንን ተጠቃሚ የሚጠ,ያደርጉ ስራዎችን በመስራት የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናለል ብለዋል፡፡

በክብረ በአሉ በተካሄደው ውይይት ኅብረብሔራዊ ፌዴራል ሥርዓት በኢትዮጵያ ለመገንባት የሚታዩ ተግዳሮቶችን በተጀመሩ የሀገራዊ ምክክሮች በመፍታት ሀገራዊ መግባባተትን መፍጠር ይኖርብናል ብለዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ