+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ወደ መንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ለመግባት የሚያስችለውን ማሰጀመሪያ መርሃ-ግብር አካሄደ፡፡
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ለኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት በሁለተኛው ዌቭ ወደ መንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም መግቢያ ይፋዊ ማሰጀመሪያ ላይ የማስገንዘብ መርሃ-ግብር አካሂደዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሀገራችን አሁን ካለችበት የተሻለች ሀገር እንዲትሆን ሲቪል ሰርቪሱን በሪፎርም ውስጥ ማሳለፍና የዘመኑን የቴክኖለጂ ውጤት ማስታጠቅ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ከምንኖርበት የተሻለ ህይወት ለመኖር የሁሉም ፍላጎት ነው ያሉት ሚኒስትሩ ሀገር እየተገነባ አዲስ እሳቤ እየተፈጠረ ሲሄድ እና ፈጣን የሀገራዊ ኢኮኖሚው እድገት ሲመዘገብ ደስተኛ ማህበረሰብ ከመፍጠርም ባሻገር ረጅም እድሜ መኖር የሚችል ማህበረሰብ መፍጠር እንደሚቻል አንስተዋል፡፡
የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ለሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ዓለም ላይ እየተስተዋሉ ያሉ የረቀቀና ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መቋቋምና ቀድሞ ምላሽ መስጠት የሚችሉ ጠንካራ ተቋማትን ለመፍጠር የሰው ሀይሉ ጊዜው የሚጠይቀውን የእውቀት ባለቤት መሆን አለበት ብለዋል፡፡
የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ ያደጉ ሀገራት የተገበሩትን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በሀገራችን ተግባራዊ በማድረግ የሀገራችንን የኢኮኖሚ እድገት ህልውና ለማረጋገጥ የሚያስችል ስርዓት ለመፍጠር እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የሲቪል ሰርቪሱ ሚና የላቀ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ የቴክኖሎጂውን አለም የሚመጥንና በማስተናገድ ለሀገር ውጤት የሚያስመዘግብ የሰው ሀይል ለመፍጠር ሪፎርሙ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አንስተዋል።
በመድረኩ ነገን የተሻለች ኢትዮጵያን ለመፍጠርና እውን ለማድረግ ሁሉም ርብርብ እንዲያደርግና በተሰጠው ጊዜ ሚኒስትር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት ተልዕኮውን አጠናቆ ማቅረብ እንዳበት የጋራ ተደርጓል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች