+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸምና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ውይይት አካሄደ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አጠቃላይ አመራሮችና ሰራተኞች በተሳተፉበት መድረክ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማን በጥልቀት በማካሄድ፣ በቀጣዩ የ2019 በጀት ዓመት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች ላይ ተወያይቷል።

በመድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ዶ/ር ፎዚያ አሚን፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደ ሀገር ሊያሳካቸው የሚገቡ ዘርፈ-ብዙ ስራዎች በእቅዳቸው መሰረት ስኬታማ ውጤት መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

አክለውም ተቋማዊ ሪፎርሙን ለማሳካት የሰው ኃይል አቅምና ምቹ የሥራ ከባቢ መፍጠር ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም፣ አሁን ላይ የተደረሰበትን ስኬት በማስፋት በቀጣዩ ዓመት የመንግሥት አገልግሎቶችን ይበልጥ ዲጂታላይዝ ማድረግና የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) መሠረተ-ልማትን ማስፋፋት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ገልጸዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሥራ አመራር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰለሞን አይነማር፤ ዓለም በቴክኖሎጂው ዘርፍ በከፍተኛ ፍጥነት እየረቀቀ ባለበት በዚህ ዘመን ተወዳዳሪ ለመሆን፣ ዕቅዶችን ከግብ የሚያደርስ አቅም በመገንባት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ሊያሳድጉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በትኩረትና በትብብር መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።

በበጀት ዓመቱ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ 420 የንግድ ተቋማት ወደ ኤሌክትሮኒክ ግብይት እንዲቀላቀሉ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን፣ በ"መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት" አማካኝነት የኦንላይን የመንግሥት አገልግሎቶችን 32 በመቶ ማድረስና የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) ተመዝጋቢዎችን ቁጥር 48 ሚሊዮን ማድረስ ተችሏል ተብሏል።

በተጠናቀቀው ዓመት የሀገር አቀፍ የሞባይል ተጠቃሚዎች ቁጥር 97 ሚሊዮን እንዲሁም የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 61 ሚሊዮን የደረሱ ሲሆን፣ 183 አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በለሙበትና ደረጃቸውን የጠበቁ ስታርትአፖች ድጋፍ አግኝተው 18,173 አዳዲስ የሥራ ዕድል የፈጠሩበት ስኬታማ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራ ተከናውኗል።

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ለ1,200 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረግ ባለፈ፣ በሐረር ከተማ ለአቅመ-ደካማ ዜጎች የሚሆኑ 12 መኖሪያ ቤቶችን በ26 ሚሊዮን ብር ወጪ የመገንባት ሥራ አጠናቆ ለአቅመ ደካሞች ያስተላለፈ ሲሆን በተለያዩ አካባቢወች ከ50 ሺህ በላይ ችግኞች መተከላቸው ሪፖርት ቀርቧል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የስትራቴጂ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ አዝማች ደሳለኝ እቅዶቻችንን ለማሳካት በተደረገው ጥረት የተገኙ ውጤቶችን በዝርዝር በማቅረብ፣ በቀጣይ ይህንን በማጠናከር የላቀ ውጤት እንደሚጠበቅ ገልፀዋል።

አክለውም ጠንካራ ጎኖችን በማስፋት ሥራዎችን በእቅድ ይዘን ከሰራን፣ በቀጣይ የምንሻውን ውጤት ለሀገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት ለማዋል ከዚህ በላይ መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል።

በመጨረሻም መድረኩን ያጠቃለሉት ከፍተኛ አመራሮች የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን በማጠናከር በአዲሱ በጀት ዓመት የአሠራር ስረአትን በማሻሻል፣ ቀልጣፋና የተቀናጀ አገልግሎት ለመስጠትና የተጀመረውን ሁለንተናዊ የሪፎርም ሥራ በጋራ ርብርብ ለማስቀጠል ጽኑ የጋራ አቋም በመያዝ ውይይቱን በስኬት አጠናቀዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ