+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች ኢኒሼቲቪ ስልጠናን ላጠናቀቁ የሚኒስቴሩ ሰራተኞች እውቅና ሰጥቷል።
እውቅና የሰጣቸው ሰራተኞች በኢትዮ ኮደርስ ኢኒሼቲቭ እየተሰጡ የሚገኙ ስልጠናዎችን ላጠናቀቁ ሰራተኞች ነው።
ዓለም የደረሰበት የዲጂታል ኢኮኖሚ ባለቤት ለመሆን በ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች ኢኒሼቲቪ ስልጠና ሁሉም እራስን በማብቃት፣ ስራ በመፍጠርና ሀብት በማፍራት የተገኘው እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያለመ ነው።
በእውቅና መስጠት መርሃ ግብሩ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የኢትዮጵያን በዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ በቀጣይ ለሚኖሩ እድሎች ዛሬ ላይ መሰረት ለመጣል በመጀመሪያ ራሳችንን በክህሎት ማብቃት አለብን ብለዋል።
ለዚህም በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ ዲጂታል ክህሎትን ማሳደግ ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ አያይዘውም የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ስልጠና ስንሰለጥን ትኩረታችን ያገኘነውን እውቀት ተጠቅመን ራሳችንን፣ ተቋማችንን፣ ሀገራችንንና አለማችንን ማገልገል የሚያስችል ብቃት ላይ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
በምንመራው ዘርፍ ላይ በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተደረገልን ያለው ከፍተኛ ድጋፍ ክፍተት እንዳይኖርና እምርታዊ ለውጥ እንድናስመዘግብ ስለሆነ ሁላችንም ተግተን መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የተዘጋጀ ብቁ የሰው ሀይል ሲኖረን ሁሉንም እናሳካለን ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ ሁሉም ተቋማት በቀጣይ እንዲህ ያለ መድረክ በመፍጠር የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ስልጠና እንዲሰለጥኑ ማድረግ እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሰልጣኖች ያገኙት ክህሎት ትልቅ አቅም እንደፈጠረላቸው በመግለጽ የተፈጠረውን ክህሎት ስራ ላይ በማዋል ውጤት ለማስመዝገብ የሚጠበቅባቸውን እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች