+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ዲጂታል የትምህርት ስርዓት ላይ ከሚሰራው ለርኒንግ ሉፕ (LEARNING LOOP) ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
የመግባቢያ ስምምነቱ በሁለቱ ተቋማት ትብብር ከፍተኛ ጥራት ያለው የዲጂታል ትምህርት ለኢትዮጵያ ተማሪዎች ለማድረስ ነው።
በፊርማ ስነ-ስርዓቱ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ትምህርት ለጠንካራ እና ተወዳዳሪ ኢኮኖሚ መሰረት ነው ፤ለዚህም ዘርፉን በቀላሉ ሊያግዙ የሚችሉ በቴክኖሎጂ የታገዙ የፈጠራ ስራዎችን የሚሰሩ ሀገር በቀል ተቋማትን መደገፍ ወሳኝ ነው ብለዋል።
ሚኒስትሩ በትምህርት የጎለበተ ማህበረሰብ ምርታማነትን እና ፈጠራን የሚያጎለብት የሰለጠነ የሰው ሃይል በመፍጠር የኢኮኖሚ እድገትን ለማፋጠን የሚኖረውን ፋይዳ የገለጹ ሲሆን በቴክኖሎጂ የተደገፈ መፍትሄዎችን በማጠናከር መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።
የመማር ተደራሽነትን በዲጂታል መድረኮች ማሳደግ፣በ AI የተጎላበተ ግላዊ ትምህርትን በመጠቀም የትምህርት ውጤቶችን ማሻሻል፣አገራዊ የልማት ግቦችን መደገፍ እንዲሁም የሀገሪቱን የትምህርት ካሪኩለም የተከተሉ የዲጂታል የመማሪያ መፍትሄዎችን በማዘጋጀት ዘላቂ ዲጂታል ትምህርትን ማሳደግ በስምምነቱ በትኩረት የሚሰሩ ስራዎች ናቸው።
የለርኒንግ ሉፕ (LEARNING LOOP) መስራች እና ስር አስኪያጂ ወጣት ኪሩቤል አክሊሉ በ2016 የትምህርት ዘመን በዲጂታል መድረኩ ከ260ሺ በላይ ተማሪዎች በዲጂታል የቲቶር አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልጽዋል።
አያይዘውም ይህንን ስራ ለመስራት ለዚህ አላማ የተዘጋጀውን ዌይብሳይት፣የዩቱዩብ ቻናል እንዲሁም ቴሌግራምና መሰል የመገናኛ አማራጮችን እንደሚጠቀሙ ገልፀው በዲጂታል መድረኮቹ በአማካኝ በቀን ከ10ሺ በላይ ተማሪዎች ሲጠቀሙ መቆየታቸውን አንስተዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች