+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር InoI የሚባል ስማርት ስልኮችንና ታብሌቶችን አምራች ኩባንያ ማናጀር ጋር በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መከሩ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዲጂታል ኢኮኖሚውን ሊያሳልጥ የሚችለውን በአለም ለረጅም አመት የኖኪያ ሞባይል ተደራሽ ሲያደርግ ከቆየው InoI የሚባል smart phone and Table ከሚያመርት ኩባንያ ጋር በኢትዮጵያ አይሲቲ ፓርክ ለማምረት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚውን የሚያሳልጡ ተግባራት ላይ የሚሰሩ ኢንቨስተሮችን ወደ ሀገር ውስጥ መተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ የመደገፍ ስራዎችን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
በሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስኬት ከጫፍ ለማድረስ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል የስማርት ስልክ ተጠቃሚ ለማድረግ አምራች ድርጅቶች በሀገር ውስጥ እንዲያመርቱና በዝቅተኛ ዋጋ ተደራሽ እንዲሆን ከአጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እንሰራለን ብለዋል፡፡
የ InoI ስማርት ስልክ (smart phone and Tablet) ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ vassili sibirtsev በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ተናግሯል፡፡
ድርጅቱ የሚያመርታቸውን ስማርት ስልኮችንና ታብሌቶች በዝቅተኛ ዋጋ ለገበያ ማቅረብ እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡
ምክክሩ ቀጣይነት እንደሚኖረውና የኢቨስትመንት ስራውን ወደ ተግባር ለማውረድ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ተቀራርበው እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች