+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በID4AFRICA 2025 እየተሳተፉ የሚገኙትን የኒጀር ሪፐብሊክ የመገናኛ እና አዲስ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር Adji Ali Salatou በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የኒጀር ሪፐብሊክ የመገናኛ እና አዲስ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር የሆኑትን Adji Ali Salatou በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን በተቋሙ ውስጥ የሚገኘውን የዳታ ማዕከልም የማስጎብኘት መርሃ ግብርም አካሂደዋል፡፡

የኒጀር ሪፐብሊክ የመገናኛ እና አዲስ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ለመጀመሪያ ግዜ የመጡ መሆኑን ገልጸው በከተማዋ ባዩት እንደተደነቁ በመግለጽ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና በዲጂታል ዘርፉ ላይ ያላትን ስኬት ልምድ ለመጋራትም ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በበኩላቸው ሀገራችን በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ዘርፍ ውጤቶች በማምጣት የሀገር እድገትና የህዝብን ህይወት ለመለወጥ ፖሊሲወችና ስትራቴጅወች ተቀርጸው እየተተገበሩና ሰፋፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ ውጤቶችም እየተመዘገቡ መሆኑን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ መዲና በቀኝ ግዛት ያልተያዘች ሀያል ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትሩ በቆይታቸው የአድዋ ድል ሙዚየምን እንዲጎበኙና አዲስ አበባን ተዘዋውረው እንዲመለከቱ ጋብዘዋል። ተቋማቸውም ሀገራዊ ኢኮኖሚውን ለማጎልበት እና የዘመነ የቴክኖሎጂ እውቀት ባለቤት ለመሆን ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በጋራ ለመስራትና ለማደግ እየሰራች ነው ያሉት ሚኒስትሩ ከኒጀር ሪፐብሊክ የመገናኛ እና አዲስ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር አብሮ ለመስራትና በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ስኬቶቻችንንም ለማጋራት ዝግጁ ነን ብለዋል።

የኒጀር ሪፐብሊክ የመገናኛ እና አዲስ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር Adji Ali Salatou በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ጋር አብሮ ከመስራትም ባለፈ ብዙ ልምድ መቅሰም እንደሚፈልጉ ተናግረው፤ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ያለች ሀገር ናት ያሉት ሚኒስትሩ

በተቋሙ ተዟዙረው ባደረጉት ጉብኝትና ምክክር ስኬታማና ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

የኒጀር ሪፐብሊክ የመገናኛ እና አዲስ የመረጃ ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በመስከረም ወር በሚያደርገው የዲጂታል ሳምንት ፎረም ላይ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ እንዲገኙ ጋብዘዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ