+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ረዳት ዋና ጸሀፊ እና የዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ልዩ ልዑክ ከሆኑት ዶ/ር አማንዲፕ ሲንግ ጊል (Dr. Amandeep Singh Gill) ጋር ተወያዩ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ከተመድ ረዳት ዋና ጸሀፊ እና ዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጅስ ልዩ ልዑክ ዶ/ር አማንዲፕ ጋር የተለያዩ የመንግስት ተቋማትን በማሳተፍ ውጤታማ መድረክ አካሂዷል፡፡

መድረኩ ዲጂታልና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂዎች አብዮታዊ አቅም በኢትዮጵያ እና በተቀረው አለም በአስተዳደር፣ በኢኮኖሚ ልማት እና በማህበረሰብ ግንባታ ላይ ያላቸውን አንድምታ ለመቃኘት ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ በተለይ ምጣኔ ሀብት እድገት፣ በቴክኖሎጂ ፈጠራና ሽግግር፤ እንድሁም በሌሎች የትብብር ማእቀፎች ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፋዊ ደንቦችን በማውጣት እና እንደ “Open-Ended Working Group for ICT እና AI Advisory Group” የመሳሰሉ መድረኮችን በመፍጠር ረገድ ያለውን ወሳኝ ሚና በመረዳት ከትርፋቶቹ ተጠቃሚ ለመሆን በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል፡:

ኢትዮጵያ በመሰረተ ልማት፣ በአስተዳደርና በሰው አቅም ግንባታ ላይ በማተኮር የዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገት የሚቀሰቅሱ ጠንካራ ፖሊሲዎችንና ተቋማትን አቋቁማለች ያሉት ሚኒስትሩ ዓለም አቀፍ አጋርነት በማሳደግ ረገድ ያለውን ተጨባጭ ጥቅም ለማሳየት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የቴክኖሎጂ ዲፓርትመንቶች ጋር ያለውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ለዚህ ራዕይ ቁርጠኛ ነች ያሉት ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በተመድ የሚኖሩ መልካም አጋጠሚወችን ሁሉ አሟጣ ለመጠቀም ያላትን ዝግጁነት ለሃላፊው አረጋግጠውላቸዋል፡፡

የ2024 አመት በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ 100 ተደማጭነት ያላቸው እና ተጸኖ ፈጣሪ ተብለው በ ታይምስ መጽሄት የተመረጡት የUN Under-Secretary General ዶ/ር አማንዲፕ በዚህ ወሳኝ ዘርፍ ስለተባበሩት መንግሥታት የስራ እንቅስቃሴዎች እንድሁም በተመድ ውስጥ የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎችን በተመለከተ ያላቸውን እውቀትና ልምድ በማካፈላቸው በሚኒስትሩ ምስጋና የተቸራቸው ሃላፊው የድቡባዊ ሃገራት በዲጂታል አለም እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑባቸውን አማራጮችና የአስተዳደር ማዕቀፎችን በማየት ይበልጡን ተሳታፊ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

ዶ/ር አማንዲፕ ሲንግ ጊል የተጀመሩ በርካታ እድሎችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎች ታዳጊ ሃገራት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ማዕቀፍ እንዲጠቀሙ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

መድረኩ ቴክኖሎጂ በኢኮኖሚ እድገት፣ በማኅበራዊ እድገትና በዓለም አቀፍ ደህንነት ላይ የሚያሳድረውን ከፍተኛ አወንታዊና አሉታዊ ተጽዕኖ የጎላ መሆኑን አጽናኦት ሰጥቶ ያስተናገደ ነበር፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙ የመንግስት ሃላፊዎችም በርካታ ጥያቄዎችን ለዶ/ር አማንዲፕ ያቀረቡ ሲሆን ለቀረቡ ጥያቄዎችም የተመድ ሃላፊው ማብራሪያዎችን ስጠተዋል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ