+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ አመራሮች የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል አገልግሎትን ጎበኙ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በአዲስ አበባ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን ተዟዙረው በመጎብኘት በጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሀገራችን የዲጂታል ዘርፉን በመጠቀም የሲቪል ሰርቪሱን ቀልጣፋና የዘመናዊ አገልግሎት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተሄደበት ርቀት ለክልሎችና ለዘርፉ ተዋናዮች በሞዴልነት የሚወሰድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኢትዮጵያ ያላትን ስፋትና የህዝብ ቁጥር ከግምት ውስጥ በማስገባት በሺዎች የሚቆጠሩ አገልግሎቶችን በፍጥነት ወደ ዲጂታል መቀየር የለውጥ ጉዟችንን ከማፋጠን ባሻገር በመንግስትና በህዝብ መካከል ጠንካራ መተማመን ይፈጥራል ብለዋል።

የቀደሙ የዜጎች ስብራቶች በዘመነ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት ማከም ይቻላል ያሉት ሚኒስትሩ የሰው ልጅን ክብር የሚመጥን ምቹ አካባቢን ፈጥረን እርካታ የሚፈጥር አገልግሎት ስንሰጥ ሀገር ወዳድ ዜጋ ማፍራት እንደሚያስችል አስገንዝበዋል፡፡

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ፍኖት ተከትሎ የዘመነ ሀገር ለመፍጠር ለሚደረገው ጥረት የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የአዲስ መሶብ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ የመሶብ አንድ ማዕከል ዲጂታል የመንግስት አገልግሎትን በማዘመንና ጊዜውን የዋጀ ቴክኖሎጂን በአግባቡ በመታጠቅ ለኢትዮጵያ ፍቱን መድኃኒት ማግኘት እንችላለን ብለዋል።

የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን በማስፋትና አዳዲስ አሰራሮችን በመጨመር፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞን ዳር ለማድረስ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በመጨረሻም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ለማሳካት የጎላ ድርሻ እያበረከተ ለሚገኘው 'አዲስ መሶብ' የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ