+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከ ጁላይ 29-30 በቤጂንግ በተካሄደው በቻይና አፍሪካ የዲጂታል ትብብር ፎረም ላያ ተሳትፈዋል።
በፎረሙ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የህዝባዊት ቻይና ሪፐብሊክ የኢንዱስትሪ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዙንግሎግ ጂን፣ ቻይና ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን ትብብር የጋራ ተጠቃሚነትን መሠረት አድርጋ አጠናክራ መቀጠል እንደምትፈልግ አስታውቀዋል ።
በዚህ ፎረም ላይ ንግግር ያደረጉት ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ ቻይና እና ኢትዮጵያ በዲጅታል ልማት እያደረጉ ያሉት ትብብር ጠንካራ መሆኑን አንስተው ይህንኑ ትብብር ወደላቀ ደረጃ ለማሳደግ ጥረት እንደሚደረግ አብራርተዋል ።
ሚኒስትሩ በተለይ ኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንሰፎርሜሽንን ለማረጋገጥ እየሰራች ያለችውን እና የተገኙ ውጤቶችን የበርካታ አፍሪካ አገሮች ሚኒስትሮች እና አምባሰደሮች በተገኙበት ፎረሙ አብራርተዋል ።
በዚሁ ፎረም ላይ የቻይና እና አፍሪካ የዲጂታል ትብብር እና ልማት የድርጊት መርሐ ግብር ይፋ ሆኗል። የድርጊት መርሃ ግብሩ በቻይና እና በአፋሪካ አገራት መካከል በዲጅታል ልማት ያለውን ትብብር ማሳደግ ነው።
ትብብሩ በዲጅታል ፓሊሲ፣በዲጅታል መሠረተ ልማት ፣ ኢኖቬሽን ፣ ደህንነት ፣ የዲጅታል ክህሎት በመሳሰሉ ጉዳዬች ላይ የሚያተኩር ነው።
የድርጊት መርሐ ግብሩ 5/6ኛ ትውልደ ቴክኖሎጂ ልማት ፣ የአርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ምርምር ማዕከላት መገንባት ፣ የቴክኖሎጂ ስታርታፖችን በኢንቨስትመንት መደገፍ እና በላቁ እና መጻኢ ቴክኖሎጂዎች ላይ የባለሙያዎችን አቅም መገንባት ይገኝበታል ።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች