+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢፌዲሪ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የተከበሩ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ከደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚኒስትር የተከበሩ ዶ/ር ብሌድ ንዚማንዴ ጋር በሁለቱ ሀገራት የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት መካካል በሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ እ.አ.አ ሰፕቴምበር 10/2021
በጋራ ለመስራት በተፈረመው ስምምነት መሰራት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ለመጎብኘት፣ ለመገምገምና ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ውጤታማነት የአስር አመት ሀገራዊ እቅድን ተግባራዊ ለማድረግ በሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን እንዲሁም ዲጂታላይዜሽን ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አንስተዋል፡፡
ሚኒስትር ድኤታው አያይዘውም በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካላት ደቡብ አፍሪካ የምርምርና ልማ፣ቴክኖሎጂ ሽግግርና ኮመርሻላይዘሽን፣ኢኖቬሽንና ኢንዱስትሪያላይዜሽን፣የሰው ሀብት ልማት፣የምርምር ባለሙያዎች ትብበር እንዲሁ የጋራ መሰረተ ልማት ዝርጋታና አጠቃቀም ዙርያ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ውጤታማነት የአፍሪካዊያንን ትብብር ማሳያ መሆኑን አንስተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ የሳይንስ፣ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሼን ሚኒስትር የተከበሩ ዶ/ር ብሌድ ንዚማንዴ ደቡብ አፍሪካ በስፔስና አስትሮኖሚ፣ በምርምርና ኮመርሻላይዜሽን፣በባዮ ኢኮኖሚ፣በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣በናኖቴክኖሎጂ እና የሰው ሀይል ልማት ያላትን ልምድ ለኢትዮጵያ ለማከፈል እና የኢትዮጵያን ልምድም ለመቅስም ዝግጁ መሆንን ተናገግረዋል፡፡
አያይዘውም በቀጣይ በናኖ ቴክኖሎጂ፣በስፔስ ሳይንስና አስትኖሚ በማቴሪያል ሳይንስ እንዲሁም በሰው ሀብት ልማት ትኩረት በመስጠት የአፍሪካን የ2063 አጀንዳ አፍሪካዊያንን በማስተባበር እንዲሁም ሀገር በቀል ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት በመስጠት መሰራት እንደሚገባ አንስተዋል።
ሁለቱ መሪዎች በአሀጉሩ የተበታተነውን የሳይንስ፣ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ስራን በተቀናጀ መልኩ መምራት ለአሀጉሩ የዘርፉ ውጤታማነት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ ያላቸውን ትብብር በማጠናከር ሌሎችን የአፍሪካ ሀገራት መሳብና ማቀናጀት እንደሚጠበቅባቸው ተግባብተዋል።
በስምምነቱ በስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በአስትሮኖሚ ሁለት ፕሮጀክቶች በባዮና ኢመርጅንግ ቴክኖሎጂ አምስት ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ሰባት ፕሮጀክቶች በሁለቱ ሀገራት ትብብር እየተሰሩ ይገኛሉ።
ከነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ በባዮና ኢመርዲንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩቱ አየተሰሩ የሚገኙ ፕሮጀክቶች የተጎበኙ ሲሆን ስራዎቹ አመርቂ ደረጃ ላይ የሚገኙ መሆኑ ተጠቅሶ ሊሰፉ እንደሚገባ ተነስቷል።
በውይይቱ ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ የጋራ ሰራዎችን ለመስራት የሚየስችል የጋራ ፈንድ በማፈላለግና በመመደብ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች