+251118132191
contact@mint.gov.et
የኢፌዲሪ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል። ==============
በኦስትሪያ ቬና እየተካሄደ ባለው የቴክኒክ ትብብር ፕሮግራም የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO) ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ሚስ ፋቱ ሀይዳራ እና ሚስተር ሲዮንግ ዦው ጋር በተለያዩ አጀንዳዎችን ላይ የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዳዲስ የማምረቻ አሰራሮችን ለመቀመር የUNIDO ድጋፍን በመጠየቅ በመካከላቸው የትብብር ጥረቶች አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሩ አፅንዖት ሰጥተው አንስተዋል።
የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO) ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች ሚስ ፋቱ ሀይዳራ በውይይቱ ላይ ለሚኒስትሩ እንደገለጹት በህዳር 2024 መጀመሪያ ሳምንት UNIDO እና የኢትዮጵያ መንግስት በጋራ ያዘጋጁትን ፕሮግራም የአለም የረሃብ ኮንፈረንስ እውቅና ሰጥተዋል ብለዋል።
እንደ ኢትዮጵያ አይነት የአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የተቀናጀ ራዕይ እና ቆራጥ እርምጃ አስፈላጊ መሆኑን ሃላፊዋ አጽንኦት የሰጡ ሲሆን ይንንም የኢትዮጵያ ጥረት ከUNIDO በኩል ለሌሎች ምሳሌ አድርገው እንደሚጠቀሙት ተገልጿል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ UNIDO የአፍሪካ የልህቀት ማእከልን ለመገንባት ኢትዮጵያን በመመርጣቸው አመስግነው ይህንኑም በሙሉ አቅም ወደሚፈለገው ውጤት ለማድረስ ከ UNIDO ጋር በቅርበት በመተባበር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ከሌላኛው የ UNIDO ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ሲዮንግ ዦው ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ፣ ቻይና እና UNIDOን ያካተተ የሶስትዮሽ ተነሳሽነት ተፈጻሚነት ያላቸውን ቴክኖሎጂዎች ለማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቶቹ ቀጣይ በUNIDO በተያዙና ለኢትዮጵያ ሊደረጉ ስለታቀዱት የማኑፋክቸሪንግ ዲጂታላይዜሽንና ኢኖቬሽን ስራወች ላይ የትብብር ስልቶችን የለዩ ሲሆን ይህንን በ UNIDO የተያዘውን የዲጂታላይዜሽን ውጥን እውን ለማድረግም የሁለትዮሽ ቡድን ተመስርቶ ዲዛይኖቹ ላይ co-work እንደሚያደርጉ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በፍጥነት ወደ ስራ ለመግባት የሰነዶች ዝግጅት እንዲደረግ ሚስተር ዦው ያነሱ ሲሆን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ኢትዮጵያ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁነቷን አረጋግጠዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች