+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኦስትሪያ ቬና እየተካሄደ ባለው የቴክኒክ ትብብር ፕሮግራም የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው።

በኮንፈረንሱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በኒውክሌር ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና አፕሊኬሽን ጉዳዮች ላይ ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረቻቸውን ስራዎችና ትብብሮች አንስተዋል።

የኒውክሌር ሳይንስ ማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ልማትን በማረጋገጥ በጤና፣ በምግብ፣ በሀይል፣ በኢንቫይሮመንት እና በማኒፋክቸሪንግ አንገብጋቢ የሆኑ አለም አቀፍ ተግዳሮቶችን በመወጣት ረገድ ያለውን ወሳኝ ሚና አጽንኦት ሰጥተው የገለጹት ሚኒስትሩ ሀገራቸው ይህንን የተረዳ እቅድ በመያዝ በመስራት ላይ መሆኗን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በተለይም የኒውክሌር ቴክኖሎጂን በመጠቀም የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር፣ የኒውክሌር ህክምናን ለማስፋፋት እና ራሱን የቻለ የኑክሌር ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል ለማቋቋም ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

እያይዘውም የአረንጓዴው ሌጋሲ ተነሳሽነት ለአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት ያለን ቁርጠኝነት ከብዙ ማሳያዎች አንዱ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ አቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ መስራች አባል እንደመሆኗ መጠን ከኤጀንሲው ለሚደረግላት ድጋፍ አመስግነው፣ ከሰውሀይል ልማት በተጨማሪ እንደ ሬይስ ኦፍ ሆፕ (Rays of Hope)፣ Atoms for Food, Zodiac, Nutec Plastics እናመሠል የኤጀንሲው ኢኒሸቲቮች እንዲሁም በማሪ ስኮሎዶቭስካ-ኩሪ ፌሎውሺፕ ባሉ ፕሮግራሞች ላይ የበለጠ ትብብር ለማድረግና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጠናከረ ግንንኙነት እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ሚኒስትሩ ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ “ሀገራት በኒውክሌር ሳይንስ በዘላቂነት እንዲታገዙ ለማስቻል IAEA በተልእኮው ላይ ለማበረታታት በምናደርገው ጥረት ተባብረን መስራት አለብን” ያሉ ሲሆን የድርጅቱ ተባባሪ አካላትና አባል ሃገራት አስፈላጊውን ትብብር እና ድጋፍ እንዲያጠናክሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

የሚኒስትሮች ስብሰባ የቀጠለ ሲሆን ሚኒስትሩ ከአለማቀፉ የባለብዙ ወገን ተቋማት መሪወች ጋር ልዩ ልዩ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉና የኢትዮጵያን ዘርፈብዙ ጥረት እንደሚያስረዱ የተገለጸ ሲሆን ይህም ተሳትፎ የበለጠ ውጤታማ አጋርነት እና አበርክቶዎች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ