+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኤሌክትሮኒክ ንግድ ስርዓትን በላቀ ደረጃ መተግበርና መጠቀም የሚያስችል አሰራር እንዲዘረጋ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ ይሹሩን ዓለማየሁ (ዶ/ር)

በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ፈጣን የአይሲቲ እድገት እያስመዘገበች ትገኛለች፡፡ ከነዚህም መካከል የሞባይል የኢንተርኔት አገልግሎት ማደግ፣ የሞባይል ተጠቃሚዎች ብዛት መጨመር እና የኢንቴርኔት ዋጋ እየቀነሰ መሄድ የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ እየሰፋ እንደሄደ ጉልህ ማሳያ ናቸው፡፡

ከዚህም ባሻገር የሳይበር ደህንነት ማዕቀፎችን ፣ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን ተጠቃሚዎች ብዛት፣ የኢ-ክፍያ እድገትን እንዲሁም የኦንላይን የመንግስት አገልግሎቶችን መስፋት የሀገገራችን በዘርፉ ቁልፍ ስኬቶች ናቸው።

የዲጂታል ፋይናሻል አካቶ ትገበራ ጥረቶችም በዚያው ልክ ፍሬ እያፈሩ ሲሆን የሞባይል ገንዘብ እንደ ቴሌብር፣ ኤም ፔሳ ያሉ ፕላትፎርሞች ዕድገት እና ፈጠራን ለማሳደግ የአይሲቲ ፓርክ በዘርፉ ወደ ስራ እንደገባ መደረጉ ተጠቃሽ ነው፡

ዘርፉን የበለጠ ለማሳደግ ፣ ከአለምአቀፍ ማዕቀፎች እንደ የአፍሪካ ነጻ ገበያ (AfCFTA)፣ ከምስራቃዊውና ደቡባዊ ቀጠና የጋራ ገበያ (COMESA)፣ እንዲሁም ከዓለም የንግድ ድርጅት (WTO) ጋር የተጣጣሙ ምቹ የአሰራር ስርአት መዘርጋት ፤በዘርፉ የቴክኒክ እውቀት ያላቸው ባሙያዎች ማፍራት ፣ በየተቋማት የተበታተኑ ህጎች ማቀናጀት፣ የአካታችነት ችግሮችና እና የሳይበር ደህንነት ስጋቶች ውጤታማ የሆነ ትግበራን እእንዲኖር ማስቻል የግድ ነው።

ከዚህ አኳያ ጠንካራ የስታንዳርድ ፖሊሲዎች፣ የኢ-ኮሜርስ የህግ ማህቀፎችንና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ፣ከኢትዮጵያ ዲጂታል ስትራቴጂ 2025 ጋር በተስማማ መልኩ መተግበር ያስፈልጋል።

በዚሁ አግባብ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከደቡብ ኮሪያ ሪፐብሊክ ሳይንስ እና አይሲቲ ሚኒስቴር ስር የሚገኘው የኮሪያ ኢንፎርሜሽን ሶሳይቲ ልማት ኢንስቲትዩት (KISDI) ጋር በመተባበር በስታንዳርድ ፖሊስና በኤሌክትሮኒክስ ንግድ የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ በቀረበ የፕሮጀክት ፕሮፖዛል መሰረት የሀገራችንን የዲጂታል ኢኮኖሚ ስነ ምህዳር የሚደግፉና የሚያሻሽሉ ሀገራዊ ደረጃዎችን፣ ፖሊሲዎችን እና መመሪያዎችን ለማዘጋጀት ድጋፍ ለማድረግ የመጡ ከፍተኛ የአማካሪዎች ቡድንን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ስራ አስጀምረዋል፡፡

እንደ ዶክተር ይሹሩን የኢትዮጵያ እና የደቡብ ኮሪያ መንግስትና ህዝብ የቆየ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው በመሆናቸው በበርካታ በይነ መንግስታዊ ትብብሮች ግንኙነታቸውን አጠናክረው መቀጠላቸውን አውስተው የደቡብ ኮሪያ መንግስት ኢትዮጵያን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ልማት እንድትጠናከር ለሚያደርገው ያላሰለሰ ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

የደቡብ ኮሪያ መንግስት ኢትዮጵያን በድጅታል ትራንስፎርሜሽን የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ በተለይም በኤሊክትሮኒክ ትራንዛክሽን፣ ኢኮሜርስና መሰል የድጅታላይዜሽን እቅዶቿን እንድታሳካ ልምዶቿንና አቅሞቿን ለማጋራት ከምታደርገው ጥረት አንዱ አማካሪ ድርጅቶችን በመቅጠር የሚደረገው ድጋፍ በቀዳሚነት ይጠቀሳል ብለዋል፡፡

‘’የኤሌክትሮኒክ ንግድ ስርዓትን በላቀ ደረጃ መተግበርና መጠቀም የሚያስችል አሰራር እንዲዘረጋ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ ‘’ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዲኤታው አማካሪ ድርጅቱ በኢትዮጵያ የተጀመረውን የኤሌክትሮኒክ ንግድ/ኢ ኮሜርስ ወጥነት ያለው፣ ማነቆዎችን የሚፈታና በተገልጋዩና ተጠቃሚው ዘንድ ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያስችል የአሰራር ስርዓት አጥነተው በማቅረብ እንዲተገበር፣ ተግዳሮቶችን እንዲፈታና ከዳበረው ዓለማቀፍ የኤሊክትሮኒክ ንግድ ስርዓት ጋር ለማስተሳሰር አቅም ይፈጥራል ብለዋል፡፡

በኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ ከ80 ሚሊዮን በላይ ሞባይል ስልክ ተጠቃሚ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የሚገኝ የኢንተርኔት ተደራሽነትና ሽፋን መኖር፣ የደጅታል መታወቂያ አገልግሎት መስፋፋት በመኖሩ የኤሌክትሮኒክ ንግድን ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ መተግበርና ለአህጉራዊና ቀጠናዊ ትስስሩን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ ለአማካሪ ቡድን አባላቱ ገለጻ ተደሮላቸቸዋል፡፡

የቡድኑ ውጤት ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ህብረት አባልነት፣ ለአህጉራዊ የንግድ ትስስር ትልሟና ለዓለም የንግድ ድርጅት አባልነት ለምታደርገው ጉዞ አሰራሩን ወጥነት እንዲኖረው የሚያደርግ ሲሆን በመስኩ ያጋጠሙትን ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ማነቆዎችን መፍታት የሚያስችል መፍትሄ እንደሚያቀርብ ይጠበቃል፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ