+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በአፍሪካ ቀዳሚው የብሎክቼይን ቴክኖሎጂን ተጠቃሚ ሆነ።

የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ፣ በብሎክ ቼን ቴክኖሎጂ ላይ መሰረት ያደረገ የውጭ ሀዋላ አገልግሎት በኢትዮጵያ ለማስጀመር InFTF ጋር በጋራ መሥራት መጀመሩን አስታውቋል።

የባንኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአካታች ፋይናንስና ማህበራዊ ተሳትፎ ላይ ከሚሠራው InFTF ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን በሀገሪቱ የመጀመሪያው የሆነውን በብሎክቼን ቴክኖሎጂ የታገዘ የሬሚታንስ አገልግሎት ለመስጠት በተካሄደው ስትራቴጂካዊ አጋርነት የብሎክቼይን አገልግሎት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጀመረ፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ / ይሹሩን አለማየሁ የብሎክቼይን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እና የኢስቶኒያው አካታች ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (InFTF ) ላደረጉት ተነሳሽነት በማድነቅ በሀገራችን ቴክኖሎጂ ለኢኮኖሚ እና ለማህበራዊ ልማት እድገት ዋና መሰረት ሆኖ የሚያገለግል መሆኑን አንስተዋል። ሀገራችን ለምታራምደው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞም ከፍተኛ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡

ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ የብሎክቼይን ቴክኖሎጂን የፋይናንስ አገልግሎት በመጠቀም የባንክ ዘርፉን አቅም ማጎልበት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው ስምምነቱ InFTF ጋር በጋራ በመሆን ፈጣን ከሬሚታንስ መላኪያ ክፍያ ከፍተኛ መሆን ጋር በተያያዘ ገንዘብ መላላክ ላይ የነበረውን ውስንነት በማስቀረት ድንበር ተሻጋሪ የሃዋላ አገልግሎቶችን፣ ተደራሽ ላልሆኑ የማሀበረሰብ ከፍሎች በበቂ ሁኔታ በማቅረብ ማህበራዊ ችግሮችን የማቃለሉን ሂደት ያግዛል ብለዋል።

ባንኩ ለዲጂታል ቴክኖሎጂ ቅድሚያ በመስጠት የማህበረሰብን ችግር መቅረፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሠራ የገለጸ ሲሆን በውጭ ሀዋላ ረገድም የመላኪያ ክፍያ ውድነትን ጨምሮ ለሚስተዋሉት ችግሮች መፍትሄ የሆነ አዲስ ስልት እንደሆነ ተገልጿል።

ባንኩ መተግበሪያውን ከፕሌይ ስቶርና አፕ ስቶር በቀላሉ በማውረድ መጠቀም እንዲቻል ለተጠቃሚዎች ከፍት መሆኑን አሳውቋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ