+251118132191
contact@mint.gov.et
የኮሪያ-ኢትዮጵያ ዲጂታል የመንግስት ትብብር ፎረም በአዲስ አበባ ተካሄደ።
የኢትዮጵያና የኮሪያ መንግስት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማሳካትና ወቅታዊ ልምድን በማጋራት ቀጣይነት ያለው ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል የተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ የመንግስት ድርጅቶችና የኮሪያ ልዑካን አባላት፣ የ ROK&KOICA ሰራተኞችና ኤምባሲ የተሳተፉበት የዲጂታል መንግስት ፎረም ተካሂዷል።
ፎረሙ በሁለቱ ሀገራት የነበረውን የረጅም ጊዜ ወዳጅነትን ይበልጥ በማጠናከር በዲጂታል መንግስት ትብብር ላይ በጋራ ለመስራት ያለመ ነው።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ የኮሪያና ኢትዮጵያ የዲጂታል መንግስት ትብብር ፎረም የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማራመድ፣ ፈጠራን ለማጎልበት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ደቡብ ኮሪያ በዲጂታል አስተዳደር ዓለም አቀፋዊ መለኪያ ሆናለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ሃይል በመጠቀም አስተዳደርን ለማሻሻል፣ የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥን ለማጎልበት እና ሁሉን አቀፍ እና ቀጣይነት ያለው እድገት ለማምጣት ባለን አንድነት የሁለትዮሽ ጉዟችን ወሳኝ ወቅት መሆኑን ገልፀዋል።
በኢ-መንግስት፣ ዜጋን ያማከለ አገልግሎት እና የመንግስት ሴክተር ፈጠራ ላይ ያስመዘገበው ውጤት አበረታች እና አስተማሪ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ግልጽ እና ተጠያቂነት ባለው የህዝብ ፋይናንስ ውስጥ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከሚያሳዩ እንደ የፊስካል መረጃ ስርዓት እና ብሄራዊ ዲጂታል በጀት እና አካውንቲንግ ሲስተም ካሉ የኮሪያ የተቀናጀ የፊስካል አስተዳደር ስርዓቶች ብዙ የምንማረው ነገር አለ ብለዋል።
በኢትዮጵያ የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደርና የአፍሪካ ህብረት ቋሚ ተወካይ ጁንግ ካንግ ኮረያ የአፍሪካን የእድገት አቅም ከፍ አድርጋ በመመልከት አዳዲስ የስትራቴጂያዊ ትብብርን ለመገንባት ጥረት በማድረግ ጠነካራና በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ የጋራ እድገትን፣ ዘላቂነትንና አብሮነትን ያማከለ የወደፊት ጊዜን እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል።
የኮሪያ የአገር ውስጥ እና ደህንነት ሚኒስቴር ዳይሬክተር በዩንግጆን ፓርክ የኮሪያ መንግስት ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ የበለጠ የበለፀገች ሀገር ሆና ወደ አለም ተወዳዳሪነት እንድትገባ በማገዝ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
ፎረሙ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን መገንባት ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ እና በሰፊው ዓለም አቀፍ ደቡብ ውስጥ ሊያስተጋባ የሚችል የዲጂታል አስተዳደር አጀንዳ መቅረጽ እንደሆነም ተጠቁሟል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች