+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የወቅቱ የAFRA ሊቀመንበር የሆኑት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከAFRA Steering Committee እና በቬና የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ቡድን ጋር ተወያዩ፤

ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ከመስከረም 2024 ጀምሮ የ African Regional Cooperative Agreement for Research, Development and Training Related to Nuclear Science and Technology (AFRA) ሊቀመንበር ሆነዉ ለአንድ አመት መመረጣቸው ይታወሳል።

ይህንን ተከትሎ ለቀጣይ ሶስት አመታት (2025-2027) ሁለት የAFRA ኮሚቴዎች (Human Resource Development and Nuclear Knowledge Management Committee(HLSC) እና AFRA Program Management and Partnership Committee (PMPC) በማዋቀር የመጀመሪያዉን የAFRA High-Level Steering ኮሚቴ ስብሰባ አድርገዋል።

በዚህም ስብሰባ የAFRA ን አፈጻጸም ከማሳደግ እና ተደራሽነቱን ከማስፋት አንፃር አባላቱ ሊከተሏቸዉ የሚገቡ መርሆችን በመጥቀስ አቅጣጫም አስቀምጠዋል::

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የAFRA ሊቀመንበር ዶ/ር በለጠ ሞላ

መቀመጫቸውን ቬና ካደረጉ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች ቡድን ጋር (Vienna Based African Group -- VbAG) ጋር ተቀራርበው በመስራት የAFRAን እንቅስቃሴዎችን በማገዝ ይበልጥ ውጤታማነታቸውን በምያግዙ እንቅስቃሴዎች ዙሪያ የጋራ ምክክር አድርገዋል:።

የምክክሩ ዓላማም በሰላማዊ መንገድ የኒውክሌር መተግበሪያዎችን ለማስፋፋት እና ለአፍሪካ ቀጠናዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ የበለጠ ለማጠናከር በሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ ሃሳቦችን ለመለዋወጥ እና አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ታስቦ የተዘጋጀ ነበር።

በምክክሩም ላይ ከሰላማዊ የኒውክሌር መተግበሪያዎች ተጠቃሚ ለመሆን የአፍሪካ ሀገራት በትብብር መስራት እንዳለባቸው የገለጹት የወቅቱ የAFRA ሊቀ-መንበር የሆኑት ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ በተለይ መቀመጫቸውን በቬና ያደረጉ የአፍሪካ አምባሳደሮች የአድቮኬሲ ስራ በመስራት፣ የተጠናከረ የትብብርና የድጋፍ ማዕቀፍ ለአፍሪካ እንዲያመጣ በማድረግ የአምባሳደሮቹ ቡድን (VbAG) ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን አብራርተዋል።

ሚኒስትሩ የAFRA ስራን እና ቀጣይ እቅዶችን ያብራሩ ሲሆን የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን በትብብር መቆም እንዳለባቸውና በአገራት ደረጃም ትኩረት ተሰጥቶት የተለያዩ ለጋሽ አካላትን የመሳብና የማሳመን ስራዎች መሰራት አስፈላጊ መሆኑንም ገልጸዋል።

በውይይቱ የሰላማዊ የኑክሌር ልማትን ፖፑላራይዝ እንዲያደርጉ እና መቀመጫቸውን በቬና ካደረጉ የኑክሌር አልሚ ሀገራት ልምዳቸውን ለአፍሪካ ሀገራት እንዲያካፍሉ፣ ስልጠና እንዲሰጡ፣የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲካሄድ ለማድረግ አምባሳደሮቹ ከፍተኛ ሚና ያላቸው መሆኑ ጠቅሰው የAFRAን እንቅስቃሴ ይበልጥ ቀርበው እንዲያግዙ የወቅቱየAFRA ሊቀመንበሩ ዶ/ር በለጠ ሞላ ጥሪ አቅርበዋል።

የVbAG ሰብሳቢ የሆኑት የቡርኪናፋሶ አምባሳደር ክብርት Maimounata Ouattara በበኩላቸው ቡድኑን በመወከል የAFRAን እንቅስቃሴ በቅርበት ለማገዝና በኑክሌር ሰላማዊ ልማት የአፍሪካን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቡድናቸው ጠንክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ