+251118132191
contact@mint.gov.et
የወቅቱ የAFRA ሊቀመንበር የሆኑት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ AFRAን በቴክኒክና በፋይናንስ ትብብር ከሚደግፉ አጋር አገራት እና ድርጅቶች (donor countries and organizations) ጋር ዉይይቶችን አደረጉ፤
AFRA (African Regional Cooperative Agreement for Research, Development and Training Related to Nuclear Science and Technology) እኤአ 1990 በአፍሪካ ሀገራት መካከል የተደረሰ የበይነ መንግስት ስምምነት ነው ።
በዋናነት አፍሪካን ከሰላማዊ የኑክሌር ሳይንስና ቴክኖሎጅ ምርምሮችና አፕሊኬሽኖች ጋር በማስተዋዎቅ በተለይም በግብርና፣ በሀይል ምንጭ፣ በጤና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በማዕድን እና በልዩ ልዩ መስኮች ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ የሰው ሀይል ልማትን ለማስፋት ታስቦ የተደረሰ ስምምነት ነው።
AFRA ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ የአፍሪካ መንግስታት በአህጉሩ የካንሰር ህክምና ማዕከላትን በማስፋፋት፣ የሰው ሀብት ልማትን ስራን በማካሄድ፣ የግብር ዘርፉን በማገዝ፣ ምርምሮችን በመደገፍና ዘርፎችን ለማገዝ በIAEA የሚደገፉ እንዲሁም ከአጋር መንግስታትና ድርጅቶች ጋር በመተባበር ልዩልዩ ስራዎች እንዲሰሩ ሲያግዝና ሲከታተል ቆይቷል።
ሀገራችን ኢትዮጵያም በተለያዩ ጊዜያት የጨረራ ህክምና ማዕከላትን ለማስፋት፣ የገንዲ ዝንብን (Tse tse fly) ለማምከንና የቁም ከብት በሽታን (ገንዲ) ለመከላከል፣ የእንስሳት ጤና ጥበቃን እና የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማዘመን እንዲሁም የጨረራ መከላከል ስራን ለማገዝ የሚደረጉ ምርምሮችና ሀገራዊ ጥረቶችን ለማገዝ ከኤጀንሲው (IAEA) የተለያዩ ስልጠናዎችን ጨምሮ የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፎችን ስታገኝ ቆይታለች።
በአፍሪካ ሀገራት የሚጀመሩ የዘርፉ ስራወች እንዲደገፉ ቋሚ የአድቮኬሲና ክትትል ስራ የሚያስፈልግ በመሆኑ ይህንኑ ለማስፋትና አቅም ለመፍጠር እንደ AFRA አይንተ የበይነ መንግስታቱ ስምምነት አስፈላጊ በመሆኑ ታምኖበት የተፈጠረ ነው።
አለማአቀፉ የአቶሚክ ሀይል ኤጀንሲ (IAEA) አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን በቬና ባካሄደበት በመስከረም 2024 ክቡር ዶ/ር በለጠ ሞላ ለአንድ አመት የAFRA ሊቀመንበር ሆነዉ እንዲያገለግሉ ሀላፊነት የተሰጣቸው መሆኑን ተከትሎ AFRAን በገንዘብ እና በቴክንክ ትብብር ድጋፍ ከሚያደርጉ ሀገራት አምባሳደሮች (በቬና ተቀማጭ የሆኑ) እንዲሁም የድርጅቶች ሀላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።
ከ ጃፓን፣ ቻይና፣ ህንድ ፣ ፓኪስታን፣ ስዊድን፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ብራዚል፣ የአዉሮፓ ህብረት (EU) አምባሳደሮች እንዲሁም ከአለማቀፉ የአቶሚክ ሀይል ኤጀንሲ (IAEA) አመራሮች ጋር ከሚያዚያ 28 እስከ ግንቦት 02/2017 ዓ.ም (May 6-9 2025) ሲያካሂዱ የቆዩትን ውይይይተ አጠናቀዋል።
በውይይታቸው የAFRAን አፈፃፃም ከማሳደግ እና ተደራሽነቱን ከማስፋት አንጻር አገራቱ እና ድርጅቶች ለ AFRA አባል ሃገራት ሲያደርጉ የቆዩትን ድጋፍ አጠናክረዉ እንዲቀጥሉ እና አዳዲስ የድጋፍ ማዕቀፎችን እንዲፈጥሩ አጽኖት በመስጠት እንዲሰራ አስገንዝበዋል።
በተለይም የአፍሪካ ሀገራት ካንሰርን ለመከላከል፣ የግብርና ምርትን ለማሳደግ፣ የሰው የህል ስልጠናን ለማሳደግ፣ የሴፍቲና ሴኩሪቲ አቅምን ለማሳደግ፣ የሚያደርጉትን ጥረት ይበልጥ እንዲደግፉ ክቡር ዶ/ር በለጠ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አጋር ድርጅቶች እና አገራቱ ለAFRA አባል አገራት የኑክለር ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ዘርፎች የሰዉ ሃይል አቅም ግንባታ፣ የላቦራቶሪ መሳሪያዎች ድጋፍ እና የቴክኒክ ትብብር ሲያደርጉ የቆዩ መሆናቸው ተጠቅሶ፣ በዉይይቱ በአዳዲስ ዘርፎችም ጭምር ድጋፋቸዉን አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉ ቃል መግባታቸዉን ለማዎቅ ተችሏል፡፡
በተጨማሪም ዶ/ር በለጠ ሞላ በሁለት የAFRA ኮሚቴዎች (Human Resource Development and Nuclear Knowledge Management Committee -- HLSC እና AFRA Program Management and Partnership Committee -- PMPC) የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ያዳመጡ ሲሆን የAFRAን አፈጻጸም ከማሳደግ እና ተደራሽነቱን ከማስፍት አንፃር አባላቱ ሊከተሏቸዉ የሚገቡ መርሆችን በመጥቀስና በቀረቡ የማጠቃለያ ነጥቦች ላይ አስተያየቶችን በመሰጠተው የቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ተችሏል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች