+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስኬት እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ የላቀ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ፣ በዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተር እና ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ዌንካይ ዣንግ (Wencai Zhang Managing Director & Chief Administrative Officer World Bank Group) የተመራውን የልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው በጋራ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ።

በውይይቱም በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተከናወኑ በሚገኙ ፕሮጀክት ስራዎች አፈጻጸም እና በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ምክክር አድርገዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስትራቴጂን በስኬት በማጠናቀቅ፣ ከሀገራዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ባለፈ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስችለውን "የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂን በመተግበር ላይ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

የአለም ባንክ ትብብር ለሀገራችን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ስኬት የላቀ ሚና እንደነበረው የገለፁት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ለሚከናወኑ ዘርፈ ብዙ ስራዎች አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብሩ ሊያጠናክር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያለች ሰፊ ሀገር በመሆኗ በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂና በኢኖቬሽን ዘርፍ የምታከናውናቸው ተግባራት ለሀገራዊ ዕድገት ብቻ ሳይሆን ለአጎራባች ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስርና ልዕልና ጭምር ፋይዳ እንዳላቸው ገልፀዋል።

የዓለም ባንክ ማኔጂንግ ዳይሬክተርና ዋና አስተዳዳሪ ዌንካይ ዣንግ (ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ላይ እያከናወነች ያለችው ሥራ የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው፣ በቀጣይም የዓለም ኢኮኖሚ ትኩረት ባደረገባቸው የቴክኖሎጂ ዘርፎች ላይ ትብብሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተከናወኑ በሚገኙ የዲጂታል ፕሮጀክት ስራዎች የአፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን የተገኙ ውጤቶች ስኬታማ መሆናቸውን በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ