+251118132191
contact@mint.gov.et
የደቡብ ትብብር ድርጅት (OSC) ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባዘጋጁት ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አውደርዕይ ጎን ለጎን በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የፓናል ውይይቶች ተካሂደዋል።
አውደ ርዕዩ በቴክኖሎጂ ዘርፍ ዕውቀትን የመፍጠር፣ የመጋራት እና የመጠቀምን ዓለም አቀፋዊ አቅምን በማሳደግ በአህጉራት ተቀራርቦ ለመስራት ያለመ ነው።
በዝግጅቱ ላይ ከቴክኖሎጂ ማሳያው በተጨማሪ ትምህርት እና ክህሎትን ማጎልበት ላይ የፓናል ውይይት ተካሂዷል ።
በፓናሉ ላይ በ OSC የስርዓተ-ትምህርርት እና የሀገር በቀል ትምህርታዊ ልማት (SEED) ዋና ፀሀፊ ዶ/ር ሹብሀንጊ ሻርማ፣ በትምህርት እና በሶስተኛው የእድገት መንገድ ላይ እንዲሁም ፣በአካባቢ-ተኮር የትምህርት ስልቶች ላይ የOSCን ራዕይ አቅርበዋል።
የናይጄሪያ የሳይንስ አካዳሚ ዋና ፀሃፊ የሆኑት ዶ/ር ኤም ኦላዶን ኦዱባንጆ በፓናል ውይይት ላይ ትምህርት እንደ ዘላቂ ልማት ምሰሶ የሚሆንበትን መንገድ አቅርበዋል ፣ በንግግራቸው የበለጠ አካታች ወደፊትን ለመገንባት የትምህርትን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተው አንሰተዋል።
በፓናሉ በቀጣይ ዘመን ኢኮኖሚ ውስጥ ዲጂታል ክህሎትን ማዳበር ወሳኝ መሆኑ የተነሳ ሲሆን በተለይ በአለምአቀፍ ደቡብ ትብብር ስር ላሉ ወጣቶች ወደ ዲጂታል የስራ ሃይል እንዲገቡ እድሎችን ሰጥቷል ተብሏል።።
በዘርፉ የተሰማሩ ኤክስፐርቶች እነዚህ እድሎች ለኢኮኖሚያዊ ማጎልበት አዳዲስ መንገዶችን በመፍጠር ረገድ ያላቸውን የለውጥ አቅም አጉልተዋል።
በፓናሉ ትምህርት ፣የፈተና አስተዳደር እና እርማት ላይ ውይይት በማድረግ የትምህርት ውጤቶችን ለማሻሻል እና ተማሪዎችን ለወደፊት ፈተናዎች በተሻለ ሁኔታ ለማዘጋጀት አዳዲስ አሰራሮችን እና መመዘኛ ስልቶችን መንደፍ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።
ለሁለት ቀናት በሳይንስ ሙዚየም የደቡብ ትብብር ድርጅት (OSC) ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን ከ14 ሀገራት የተውጣጡ 41 አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የሚቀርቡበትን አለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አውደርእይ እንድትጎበኙ ተጋብዛችዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች