+251118132191
contact@mint.gov.et
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ5 ሚሊየን ኢትዮጵያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ አፈጻጸምን ላይ ምልከታ ተካሂዷል።
በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ፕሮግራም ለመከታተልና ለመደገፍ የተቋቋመው የፌደራል ስልጠና ድጋፍና ክትትል ቡድን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን አፈጻጸም ምልከታ አካሂዳል።
ቡድን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የስልጠና አፈጻጸም ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመገምገም መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋት እንዲሁም ተግዳሮቶችን ለመፍታት ከሚመለከተው አካል ጋር በመቀናጀት መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በጋሞ እና ወላይታ ዞኖች ስልጠናው በሚሰጥበት ቦታ ከክልሉ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ሃላፊዎች ጋር በመሆን ተዟዙሮ ተመልክቷል።
በክልሉ አበረታች እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ቡድኑ ያመላከተ ሲሆን ግቡን ከዳር ለማድረስ እንደ ትልቅ ተግዳሮት የተነሱ ጉዳዮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እንዲሰራ አቅጣጫ ተሰጥቷል።
በቀጣይም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሀገራዊውን እቅድ ለማሳካት የስራቸው አካል በማድረግ እና የክልሉን ህዝብ ስለ ፕሮግራሙ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ በማድረግ የታሰበውን እቅድ ከግብ ማድረስ እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።
የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችለውን ነጻ የኦንላይን ሥልጠና እድሎች ተጠቃሚ ለመሆን https://ethiocoders.et/ በዚህ ሊንክ ላይ ይመዝገቡ።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች