+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የዲጂታል ሽግግር ጉዟችንን በማሳደግና በማፍጠን የማይበገር የንግድ ተወዳዳሪነት ለመገንባት የኔዘርላንድ ትረስት ፈንድ ፕሮጀክት የላቀ ሚና እንደነበረው ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ ገለፁ።

የኔዘርላንድ ትረስት ፈንድ 5 (NTF V)ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ከJuly 2021 - 2025 በኔዘርላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና በአለም አቀፍ የንግድ ማእከል መካከል ባለው አጋርነት ላይ የተመሰረተው በዲጂታል ቴክኖሎጂዎች እና በግብርና ንግድ ዘርፎች ውስጥ ሲያከናውን የቆየውን መርሃ ግብር የተመለከተ የመዝጊያ ፕሮግራም አካሄደ።

በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን ዓለማየሁ የኔዘርላንድ ትረስት ፈንድ 5 (NTF V) ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ወቅታዊ እና ለውጥ ላይ መሰረት በማድረግ ከሀገራዊ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች ጋር መጣጣም ብቻ ሳይሆን በተለያዩ ተጨባጭ መንገዶች እድገታችን ላይ ላበረከተው ንቁ አስተዋፅዖ ምስጋና አቅርበዋል።

የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን (STI) ፖሊሲያችንን በመደገፍ፣ የፖሊሲው ማዕቀፍ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ኢኮኖሚ ራዕያችንን ያቀፈ እንዲሆን በማገዝ፣ የላቀ የምርምርና ፈጠራ እንዲደረግ፣ አዳዲስ ስራ ፈጠራ እንዲተገበር እና ዘርፈ ብዙ ትብብር ሀገራዊ እድገትን የሚያራምዱበት ውጤቶች እንዲገኙ ከፍተኛ ሚናውን እንደተወጣ አስታውሰዋል።

የኔዘርላንድ ትረስት ፈንድ 5 (NTF V)ኢትዮጵያ ፕሮጀክት የውጭ አቅርቦት ዘርፍ ልማት፣ የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ማህበር መመስረት እና ለአፍሪካ ፌደሬሽን ለውጭ አገልግሎቶች የሚደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ የውጭ ንግድ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያላትን ህልውና በማስቀጠል ረገድ ጉልህ ክንዋኔዎችን መተግበሩን ገልፀዋል።

የቴክኖሎጂ ስታርታፖችን በማበረታታት ረገድ ከ50 በላይ የቴክኖሎጂ ስታርታፖችን እና የአይቲ/ቢፒኦ ኩባንያዎች ድጋፍ አግኝተዋል፣ የንግድ ሞዴሎቻቸውን እንዲያጠናክሩ፣ ጥንካሬያቸውን እንዲያሳድጉ እና ለአለም አቀፍ ገበያዎች ወሳኝ ተሳትፎ እድል መፈጠሩን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአለም አቀፍ መድረኮች እና የንግድ ተልእኮዎች እንድትሳተፍ በማመቻቸት ፕሮጀክቱ ለስራ ፈጣሪዎቻችን፣ አዳዲስ ፈጠራን በማበረታታት እና ኩባንያዎች በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲገናኙ፣ እንዲማሩ እና እንዲወዳደሩ አዳዲስ እድሎችን ፈጥሯል ብለዋል።

ኢትዮጵያ የዲጂታል እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳና ላይ ትገኛለች ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች እየመራን እና አሁን ወደ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እየተሸጋገረ ባለበት ወቅት፣ አገራችን ቴክኖሎጂን ሁሉን አቀፍ የእድገት ተቋቋሚነት እና የአለም አቀፍ ተወዳዳሪነት አንቀሳቃሽ ለማድረግ እየሰራች መሆኑን በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ አንስተዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ