+251118132191
contact@mint.gov.et
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ግብን ለማሳካት በኤሌክትሪክ ኃይል ቴክኖሎጂዎች ላይ በትብብር መስራት እንደሚገባ ዶ/ር በለጠ ሞላ ገለፁ፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቻይና ደቡባዊ ግሪድ ቴክኖሎጂ እና ከኢዳን ፓወር ቡድን ጋር በመተባበር የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ የሚያፋጥኑና የኃይል ዘርፉን የሚያዘምኑ የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ወደ ሀገር ውስጥ ለማምጣት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ዳር ለማድረስ ዘመናዊና ተደራሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ቴክኖሎጂዎች የማይተካ ሚና እንዳላቸው ገልፀዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ራዕይን ለማሳካት መንግሥት የግሉን ዘርፍና የዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ተቋማትን ያሳተፈ ጠንካራ አጋርነት ለመፍጠርና ምቹ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ያለው ቁርጠኝነት የላቀ መሆኑን አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ዘመናዊ የኃይል ግሪድ እና የንጹህ ኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሀገር ውስጥ በማስገባትና በማልማት የኤሌክትሪክ ኃይልን ተደራሽነት ለማስፋፋትና የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማጠናከር የሚያስችል ስልታዊ ትብብር ላይ እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡
የቻይና ሳውዘርን ፓወር ግሪድ ከፍተኛ ተወካይ ዣኦ ዚዪ የኢትዮጵያን ሰፊ የኃይል ልማት አቅምና ምቹ ፖሊሲዎች በማድነቅ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂና ልምዳቸውን ለማጋራት ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
የኤዳን ኤሌክትሮ ፓወር ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ እድሪስ አደም፤ የኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ሽግግር ለማፋጠን የግሉ ዘርፍ ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በሁለንተናዊ ዘርፍ ላይ የሚያደርገው የተቀናጀ ትብብር ስኬታማ ውጤቶችን እያስመዘገበ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የቴክኖሎጂና የልምድ ሽግግር ትብብሩ የኢትዮጵያን የኃይል ዘርፍ በቴክኖሎጂ ለማዘመን፣ የዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጠናከር እና የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ጉዞን በፍጥነት ለማሳካት አስፈላጊ መሠረት እንደሚሆን ተጠቁሟል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች