+251118132191
contact@mint.gov.et
የዲጂታል ኢኮኖሚን ፍትሃዊ፣ ሁሉን አቀፍና አሳታፊ ለማድረግ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን (STI) ዘርፍ የስርዓተ-ፆታ እና ማህበራዊ አካቶ ትግበራ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮችን አካቶ ትግበራ ለማጠናከር ያለመ ስልጠና አካሄደ።"
የስልጠናውን መርሃ ግብር በመክፈት ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ዶ/ር ፎዚያ አሚን፣ በሀገራችን የSTI ዘርፍ ውስጥ የስርዓተ-ፆታ አካቶ ትግበራን ማጎልበት ዜጎች ከዲጂታል ኢኮኖሚ ፍሬ በፍትሃዊነት እንዲጠቀሙ አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል።
የዘርፉ ተቋማት የሥርዓተ-ፆታና ማህበራዊ ጉዳዮችን በዕቅድ ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት ውስጥ በማዋሃድ፣ ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ስትራቴጂካዊ አመራር እንዲሰጡ አሳስበዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ገብረስላሴ በበኩላቸው፣ በSTI ዘርፍ ብቁ ሴቶችን ለማፍራት የስርዓተ-ፆታ ፍትሃዊነት ላይ ጥልቅ ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሴቶችን አቅም ማጎልበት ለስርዓተ-ፆታ እኩልነት ብቻ ሳይሆን ለሀገር አቀፍ የቴክኖሎጂ እድገት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት ስራ አስፈፃሚዋ ሴቶች በቴክኖሎጂ ስራዎች ውስጥ ጎልተው እንዲወጡ በትኩረት መስራት እንደሚገባ አንስተዋል።
በተጨማሪም ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞችና አረጋዊያንና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች በቴክኖሎጂ ትግበራ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ለማጠናከር ቀጣይነት ያለው የክትትልና ድጋፍ ስራዎች መካሄድ እንዳለባቸው ተናግረዋል።
በስልጠናው መድረክ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ማብራሪያ የተሰጣቸው ሲሆን፣ ተሳታፊዎች እንደዚህ ያሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳላቸው ገልፀዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች