+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የዲጂታል ዘመንን ውስብስብ ነገሮች በምንመራበት ጊዜ የኢንተርኔትን ተግዳሮቶች እየፈታን የለውጥ ሃይልን ለመጠቀም መተባበር አስፈላጊ ነው። ዶ/ር በለጠ ሞላ

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት እየተካሄደ የሚገኘው 13ኛው የአፍሪካ የኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ "Building our Multistakeholder Digital Future" በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UN-ECA) በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ጉባኤው ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ይህ መድረክ በመላው አፍሪካ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ግልጽ ውይይት ለማድረግ ወሳኝ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል።

አፍሪካውያን በተመጣጣኝ ዋጋ እና አስተማማኝ የኢንተርኔት ግንኙነት በማጠናከር የዲጂታል ሊትረሲ እና የክህሎት ልማትን በማስተዋወቅ በዲጂታል ኢኮኖሚ ውስጥ ግለሰቦችን እና የንግድ እንቅስቃሴዎችን በማጎልበት የሳይበር ደህንነትን እና የመረጃ ጥበቃን በማጠናከር አህጉራችንን በዘርፉ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በ2022 ስኬታማውን የዓለም አቀፉ IGF ኮንፈረንስን ማስተናገዷን ያስታወሱት ሚንስትሩ በፓን አፍሪካ የትብብር እና የአንድነት መንፈስ ከፊታችን ያሉትን ተግዳሮቶች በማሸነፍ ለሁሉ፤ም ብሩህ እና አካታች የዲጂታል ጊዜን ደወደፊት መገንባት እንደሚቻል ጽኑ እምነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

ሚንስትር ከተለያዩ ሀገራት የተደገኙ ተሳታፊወች በአዲስ አበባ ከተማ በሚቆዩበት ጊዜ ሁሉ የከተማዋን ውበቶች ተዘዋውረው እንዲመለከቱና የሚጎበኙ ቦታወችን እንዲጎበኙ አበረታትተዋል።

በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UN-ECA) ዋና ስራ አስፈፃሚ ሚስተር ክላቨር ጋቴቴ (Claver Gatete) የኢትዮጵያ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የአፍሪካን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በየ ጊዜው ለሚያሳዩት ቁርጠኝነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እንደ ልማት ማበረታቻ ይገባል ያሉት ዋና ስራ አስፈጻሚው የአፍሪካ ዲጂታል ጉዞ በየአመቱ 919 ቢሊዮን ዶላር በ 856 ሚሊዮን ሒሳቦች የሚያስተናግዱ እንደ የሞባይል ገንዘብ ሥርዓቶች ያሉ አዳዲስ ፈጠራዎችን በመጠቀም የዲጂታል ኢኮኖሚውን በማስተናገድ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደተግዳሮት ከ800 ሚሊዮን በላይ አፍሪካውያን ከኢንተርኔት ውጭ በመሆናቸው ከዲጂታል ኢኮኖሚው ግዙፍ እድሎች የተገለሉ ናቸው ያሉት ዋና ጽሃፊው ይህንን ለመፍታት አፍሪካውያን በጋራ መረባረብ ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ