+251118132191
contact@mint.gov.et
የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬቶች መሠረታቸው ግልጽ እና አሳታፊ ስትራቴጂ በአገር ደረጃ የተቀናጀ አመራር እና ያልተቋረጠ ግምገማ ውጤት ነው።ዶ/ር በለጠ ሞላ
ዛሬ በተከፈተው የአይዲ ፎር አፍሪካ (ID4Africa) መክፈቻ ውይይት ላይ በተወያይነት የተሳተፉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬቶችን እና በኢትዮጵያ ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ላይ የፋይዳ መታወቂያ ያመጣውን ለውጥ አንዲሁም በቀጣይ የሚጫወተውን ሚና አብራርተዋል።
በተለይም ፋይዳ መታወቂያ ፣ የዲጅታል ክፍያ ስርአት፣ የዳታ መለዋወጫ እና ማጋሪያ ስርአቶች እና የአድራሻ ስርአቶች በተቀናጀ የዲጅታል ፐብሊክ መሠረተ ልማት አግባብ በመቀናጀት የኢትዮጵያን የዲጅታል ትራንስፎርሜሽንን ይበልጥ እንዲያሳልጡ እንደሚያደርግ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
የዳጅታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬቶች መሠረታቸው ግልጽ እና አሳታፊ ስትራቴጂ በአገር ደረጃ የተቀናጀ አመራር እና ያልተቋረጠ ግምገማ ውጤት ነው ያሉት ሚኒስትሩ በቀጣይ የዲጅታል ኢትዮጵያ 2030 ባለፉት አምስት አመታት የተገኙ ልምዶችን እና ውጤቶችን መሠረት በማድረግ፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ እድገቶችን እና አዳጊ አገራዊ ፍላጎቶችን እና አለማቀፋዊ ሁኔታዎችን መሠረት በማድረግ ይተገበራል ብለዋል።
ከኢትዮጵያ ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን ልምዶች የዲጅታል ኢትዮጵያ ስኬት መሠረቶች የሆኑት ግልጽ እና አሳታፊ ስትራቴጂ ፣ ሀገራዊ ቀዳሚ አጀንዳወችን መለየት በነሱ ላይ ትኩረት ያደረገ አተገባበር መተግበር፣ በአገር ደረጃ የተቀናጀ አመራር እና ያልተቋረጠ ውጤት እንዲሁም አስቻይ የህግ ማዕቀፎች መቀረጻቸው እንደ ትምህርት ሊወሰዱ እንደሚገባ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች