+251118132191
contact@mint.gov.et
የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ አፈጻጸምን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ፕሮግራም ለመከታተልና ለመደገፍ የተቋቋመው የፌደራል ስልጠና ድጋፍና ክትትል ቡድን የድሬድዋ ከተማ አስተዳደር አፈጻጸም ላይ ምልከታ አካሂዳል።
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የ5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደርስ አፈጻጸም ዙሪያ ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ የካብኔ ጉዳዮች እና የከንቲባ ጽ/ቤት ሀላፊ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጄንሲዎች ጋር ውይይት አድርጓል።
ከተማ አስተዳደሩ ኢንሼቲቩን ውጤታማ ለማድረግ ከባድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ በሱፐርቪዥኑ ለማረጋገጥ ተችሏል።
ከዚህ ጎን ለጎን የሱፐርቪዥን ቡድኑ ወጣቶች የኮደረስ ስልጠና እየወሰዱበት ያሉትን ማዕከላት እና ዳታ ሴንተር ላይ የአካል ምልከታ አካሂዷል።
ከተማ አስተዳደሩ በአምስት ሚሊዮን ኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ላይ ሰርቲፊኬት ያገኙትን ወጣቶች ከካምፓኒዎች ጋር በማገናኘት የስራ ዕድል እንዲፈጥራላቸው እያደረጉት ያለው ጅምር እንቅስቃሴ እንዳለ ገልፆል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች