+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የገበሬውን እና የግብርና ቢዝነሶችን ኮንትራት እንዲሁም የፋይናንስ ተደራሽነት መረጃዎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አግሪ ውል ከተሰኘና የበጊዜ ኦፕቲማክስ እህት ኩባንያ ከሆነ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

የስምምትነቱ አላማ በገበሬው እና በግብርና ቢዝነሶች መካከል የሚደረገውን ኮንትራት እንዲሁም የፋይናንስ ተደራሽነት መረጃዎችን ዲጂታላይዝ ማድረግ ነው።

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በዚህ ወቅት እንዳሉት የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞን ለማሳካት በሁሉም ዘርፍ የግሉን ሴክተር በማሳተፍ ጠንካራ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል።

በዚህ ስምምነት በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ውስጥ አንድ ሚሊዮን የግብርና ኮንትራቶችን ዲጂታል በማድረግ የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ ለመደገፍ ይሰራል ያሉት ሚኒስትሩ ከዲጂታል ኢትዮጵያ አገራዊ ግቦች ጋር በማጣጣም የግብርናውን ዘርፍ ለመለወጥ ትልቅ እድል ያለው ስምምነት ነው ብለዋል።

በስምምነቱ መሰረት በግብርናው ዘርፍ የሚከናወኑ ስራዎችን ለማጎልበት እና ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ሂደቶችን ለማመቻቸት እንዲሁም ዘመናዊ የመረጃ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ይሰራል።

በስምምነቱ ላይ የአግሪ ውል መስራችና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘሩባቤል ክበበ እንዳሉት አገልግሎቱ የኢትዮጵያ የግብርና ኮንትራት ህግንና የሌሎች ባለድርሻ አካላት ፍላጎቶች ጋር የተጣጣመ ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ የዲጂታል የመረጃ ስርዓት ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

ቴክኖሎጂውን በብቃት ለመጠቀም ለባለድርሻ አካላት ስልጠና እና ድጋፍ መስጠት፤በግብርናው ዘርፍ የሚሰሩ የዲጂታል ስራዎችን በመስራት ረገድ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማቅረብና የአግሪ ቢዝነስ የቴክኖሎጂ እድገትን መደገፍ እንዲሁም የአሰራሩን ወቅታዊነት በጠበቀ መልኩ ማሻሻል እና ቀጣይነት ያለው ጥናት የማካሄድ ስራ ይሰራል ብለዋል።

በሚሊዮን የሚቆጠሩ አርሶ አደሮች ኑሮን ለማሻሻልና የፋይናንስ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የዘርፉን የዲጂታል ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ለማጠናከር በተጀመረው በዚህ ስራ የግብርናውን ዘርፍ የዘመናዊ መረጃ ከማደራጀት ባለፍ የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እንደሚያግዝ ተጠቁሟል

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ