+251118132191
contact@mint.gov.et
የግሉ ዘርፍ ተቋማት የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ያላቸው በመሆኑ ይህንኑ እንዲወጡ በጋራ በትብብር መስራት ያስፈልጋል። ዶ/ር በለጠ ሞላ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ፈጠራን ለማስፋፋት የሚያስችሉ የመግባቢያ ስምምነቶችን ከግሉ ዘርፍ ተቋማት ጋር ተፈራርሟል።
ስምምነቱ ከሳይበር ዘብ ኮንሰልቲንግ ፣ከኮርፖ መረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ( ICTET) የዘርፍ ማህበር እንዲሁም ኑና ኢትዮጵያ ከተሰኙ የግሉ ዘርፍ ድርጅቶች ጋር የተከናወነ ነው።
በስምምነቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ፈጠራ ስራን ለማበረታታት የሚያስችሉ በርካታ ስራዎች በመሰራት ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው የግሉ ዘርፍ ተቋማት የኢትዮጵያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን ለማድረግ ከፍተኛ ሚና ያላቸው በመሆኑ ይህንኑ እንዲወጡ በጋራ በትብብር መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የኢትዮጵያን አገራዊ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ፈጠራ ግቦችን ለማሳካት ስምምነቱ ያለውን ፋይዳ ያመላከቱት ሚኒስትሩ "በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ካሉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር በመስራት ዘላቂ የሆነ ዲጂታል ኢኮኖሚ ለመፍጠር፣ የዘርፍ እድገትን ለማሻሻል እና የማይበገር የኢኖቬሽን ስነ-ምህዳር ለመገንባት አላማ አለን" ብለዋል።
ሚኒስትሩ አያይዘውም እነዚህ ስምምነቶች ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና በፈጠራ ቀጣናዊ መሪ ለመሆን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ ጉልህ እርምጃ እንደሚኖራቸው እና የግሉ ዘርፍ ተቋማትም በንቃት እንዲሳተፉ እንደሚያስችል ገልጸዋል።
በስምምነቱ ላይ የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጥረት ለማጠናከር እና አገራዊ የሳይበር ደህንነት እርምጃዎችን ለማሳደግ የተካሄደው ትብብር ፤ ለዘላቂ ዕድገት ጠንካራ የዲጂታል መሠረተ ልማትን በማስተዋወቅ ኢትዮጵያ ከሳይበር አደጋዎች የመቋቋም አቅምን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የሳይበር ዘብ ኮንሰልቲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ወንዶሰን ጌታቸው ተናግረዋል።
ከኮርፖ መረጃና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ( ICTET) የዘርፍ ማህበር ጋር የተደረገውን ስምምነት በማስመልከት የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ይልቃል አባተ የአይሲቲ ኢንዱስትሪውን ለማዘመን፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናን ለማሻሻል እና ንግዶችን ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን እንዲያሟሉ ፈጠራዊ መፍትሄዎችን ለማበረታታት እንዲሁም የአይሲቲ ሴክተሩ የኢኮኖሚ ልማትን ለማጎልበት ያለውን ሚና ገልፀው ድርጅታቸው ፈጠራ ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የኑና ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ብርሃኑ ዘርጋው በኢትዮጵያ የወጣቶች ስራ ፈጠራን ለማሳደግ እና የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል የሚያስችሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም፣ በዘርፉ ለወጣቶች የክህሎት ልማት እና የስራ እድል ለመፍጠር እንዲሁም በግብርናው ዘርፍ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመፍትሄ ሃሳቦችን በማስቀመጥ፣በኢትዮጵያ የግብርና ኢንዱስትሪ ውስጥ ምርታማነትን እና ዘላቂነትን በማጎልበት እድገትን ለማምጣት ያለመ ስምምነት መሆኑን ተናግረዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች