+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የጎግል ፕሌይ የአፕሊኬሽን አልሚዎች ምዝገባ (Google Play Console) ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል መጀመሩ ለኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ ተጽእኖ የሚፈጥር ነው። ዶ/ር በለጠ ሞላ

የጎግል ፕሌይ አልሚዎች ምዝገባ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል ጀምሯል።

ይህ ምዕራፍ የሀገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ተሰጥኦ ባለቤቶች መተግበሪያዎቻቸውን በዓለም ላይ ካሉት ትላልቅ ዲጂታል መድረኮች ላይ እንዲያትሙ አዲስ እድሎችን ይከፍታል።

በጉዳዩ ዙሪያ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ መንግስት የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለመገንባት በርካታ ተነሳሽነቶችን በመተግበር እየሰራ መሆኑን ገልጸው ይህ አዲስ ጅማሮ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ነው ብለዋል።

የጎግል ፕሌይ የአልሚዎች ምዝገባ ኢትዮጵያውያን አልሚዎችን መቀበል መጀመሩ ለኢትዮጵያን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ያሉት ሚኒስትሩ ይህንን እድል ተጠቅመው የዘርፉ ባለሙያዎች ችግር ፈቺ መተግበርያዎችን በማልማት በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ሂደት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚኒስትሩ እድሉ Google ካምፓኒ ኢትዮጵያን እንዲያካትት በተደረገ ጥረት የመጣ ውጤት መሆኑንም አንስተዋል።

በሚኒስቴሩ አማካሪ የሆኑት አቶ ሰለሞን ሙሉጌታ ለኢትዮጵያውያን ስታርታፖች ምቹ ሥነ-ምህዳርን ለማዳበር ከሚተገበሩ ሰራዎች መካከል በአለም አቀፍ የዲጂታል መድረኮች እንዲሳተፉ የሚያስችሉ አለማቀፋዊ ግንኙነቶችን ማጠናከር ወሳኝ በመሆኑ እድሉን ለማመቻቸት የተለያዩ ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ተናግረዋል።

እያይዘውም ይህ አዲስ እድል ኢትዮጵያውያን ገንቢዎች የGoogle Playን አለምአቀፍ ታዳሚዎች በቀጥታ በማስገኘት መተግበሪያዎቻቸው ሰፊ እይታን እንዲያገኝ እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆን ያስችላል ብለዋል።

የሀገር ውስጥ ገንቢዎችን በማበረታታት ከአካባቢው፣ከማህበረሰቡ ወግና አኗኗር ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን መተግበሪያዎች በማልማት እንዲሁም ለአለማቀፍ ገበያው የሚመጥን ስራ ለመስራት አቅም ያላቸውን የዘርፉ ባለሞያዎች ያበረታታል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ