+251118132191
contact@mint.gov.et
የጨረራና ኑክሌር ቴክኖሎጂዎች ለሰው ልጆች የሚያበረክቱት ጥቅም
ለጨረራ በመጋለጥ የሚገኙ ጥቅሞችን በማይገድብ አግባብ ሰዎች ከጨረራ እንዲጠበቁ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል፡፡
ዛሬ ላይ በኑክሌር ፋሲሊቲዎች እና አክስለሬተሮች በሰው ሰራሽ መንገድ የሚመረቱ ራዲዮኑክላይዶች በስፋት ጥቅም ሲሰጡ ይስተዋላሉ፡፡ እነዚህ የጨረራ ቁሶች በዓለማችን ዙሪያ ለህክምና፣ ኢንዲስትሪ፣ ግብርና ምርምርና ትምህርት ዓላማዎች አገልግሎት ላይ ይውላሉ፡፡
የጨረራና ኑክሌር ቴክኖሎጂ በሰለጠነ ማህበረሰብ ውስጥ በተጨባጭ የሚስተዋሉ ሰፋፊ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያገለግል ብቻ ሳይሆን ለማህበራዊና ኢኮኖሚ ዘርፎቻችን እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡
ባለንበት ዘመን ጨረራ ለሰው ልጅ የተለያዩ ጥቅሞችን በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከነዚህ አገልግሎቶች ውስጥ በህክምና፣ ትምህርት፣ ኢንዱስትሪና የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ዘርፎች የሚሰጣቸው ጥቅሞች ተጠቃሽ ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪም ጨረራ በግብርና፣ በአርኪዮሎጂ ምርምር ስራዎች የቅሪተ-አካላትን ዕድሜ ለማወቅ (Carbon dating)፣ የህዋ ምርምር ለማካሄድ (Space exploration)፣ በወንጀል ምርመራ ስራ የህግ ተፈጻሚነትን ለማሳለጥ (law enforcement)፣ የማዕድን ፍለጋን ጨምሮ የምድርን አወቃቀር፣ ዝግመተ-ለውጥ ሂደትና በምድር ስርዓት ውስጥ ያሉ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም የተፈጥሮ ማዕድናትና የሀይል ምንጭ ሃብቶችን ለማጥናት (Geology including mining) አገልግሎት ከመስጠቱም ባሻገር ሌሎች ጥቅሞችም አሉት፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን የጨረራ ጥቅሞች ገቢራዊ ለማድረግ የጨረራ አመንጭ መሳሪያዎች ወይም ቴክኖሎጂዎች በብዙ ዘርፎች የተለያዩ ዓላማዎችን ለማሳካትም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ይደረጋል፡፡
ታክኖሎጂው የሚኖረውን አሉታዊ ተጽዕኖ በቀጣይ ጽሁፎች የምናደርስ ይሆናል።
#የኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ባለስልጣን
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች