+251118132191
contact@mint.gov.et
የጨረራና ኑክሌር ቴክኖሎጂዎች አሉታዊ ተጽዕኖዎች
ጨረራ ለሰው ልጅ የሚሰጣቸው ዘርፈ-ብዙ ጥቅሞች ቢኖሩም በአግባቡ ጥቅም ላይ ካልዋሉ የጎንዮሽ ጉዳቱ የከፋ ነው፡፡
ጨረራ በኢንዱስትሪዎች ውስጥ ጥቅም ላይ በሚውልበት ሂደት የሚከሰቱ የጨረራ ተጋላጭነት አደጋዎች፣ በህክምናው ዘርፍ ጨረራ በሽታን በመመርመርና ማከም ወቅት የሚፈጠር የጨረራ ተጋላጭነት፣ ስርዓት ያልተከተለና ጥንቃቄ የጎደለው የራዲዮአክቲቭ ዝቃጭ አያያዝና አወጋገድ ለተለያዩ የጤናና ተያያዥ ችግሮች ያጋልጣሉ፡፡
በጨረራ ምክንያት በአካባቢ ላይ የሚፈጠር ብክለትም አንዱና ዋናው ችግር ሆኖ ይወሰዳል፡፡ በጨረራ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች በህዝብ ንብረትና አካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳያስከትሉ የጨረራ ጥቅምና ጉዳትን በሚያቻችል አግባብ (striking a balance) የጨረራ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡
የጨረራ ተጋላጭነት አደጋዎችን በብቃት መቆጣጠር ወይም መከላከል የሚቻለው ደግሞ የጨረራ ቁጥጥር ስራን ማስተግበር የሚያስችሉ የጨረራ ቁጥጥር ማዕቀፎች፣ የመከላከል ስራውን የሚያሳልጡ አዋጆች፣ ህጎችና ደንቦች በተሟላ መልኩና በቁርጠኝነት ተፈጻሚ ሲሆኑ ነው፡፡
የቁጥጥር ስራው ህጋዊ ተፈጻሚነትን ጨምሮ ውጤታማ እንዲሆን የጨረራ ቁጥጥር ባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት፣ ዘመኑ ያፈራቸው አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የዘርፍ ዕድገቶችንና የቁጥጥር ስራዎች ፍላጎትና አድማስን በዓይነት መለየትና የባለድርሻዎችን ተሳትፎ ማረጋገጥ ቀዳሚ ተግባራት ይሆናሉ፡፡
መላው የባለስልጣን መ/ቤቱ ሰራተኞች ባለስልጣን መ/ቤቱ በህግ የተሰጠውን ስልጣንና ተግባር በብቃት ይወጣ ዘንድም ያላሰለሰ ጥረት ሊያደርጉ ብዙ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በዚሁ አግባብም ከጨረራ ተጋላጭነት ደህንነቱ የተጠበቀ ህብረተሰብ አካባቢና ንብረት እንዲኖር ማድረግ ይቻላል፡፡
ይቀጥላል.....
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች