+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የፀረ ጾታዊ ጥቃት፣ የአካል ጉዳተኞችና የህፃናት ቀን ተከበረ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት በሀገራችን ለ20ኛ ጊዜ የፀረ ጾታዊ ጥቃት፣ ለ20ኛ ጊዜ የህፃናት ቀንና ለ33ኛ ጊዜ የአካል ጉዳተኝነትን ቀን በጋር በፓናል ውይይት አክብረዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ኤልሳቤጥ ገብረስላሴ በተቋማችን ሦስቱንም ቀናት በአንድነት ስናከብር ትኩረታችንን የአለም እድገት መሰረት የሆነው ቴክኖሎጂ ላይ አካቶ ትግበራን ለማጎልበት ያለመ ነው ብለዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ለ20ኛ ጊዜ የፀረ ፆታዊ ጥቃት ቀን ‘’ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ’’፣ የአካል ጉዳተኞች ለ33ኛ ጊዜ ‘’አካል ጉዳተኝነትን የሚያካትት ማህበረሰብን መገንባት ለተሻለ ማህበራዊ እድገት’’ እና የህፃናት ቀን ለ20ኛ ጊዜ ‘’የህፃናት ጥበቃና የመጫወት መብት ለሁሉም ህፃናት’’ በሚሉ መሪ ቃሎች እንደሚከበሩ ጠቅስው በእያንዳንዱ ላይ ሁሉም ግንዛቤ ሊኖረው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የሴቶች እና ህፃናት ጥቃት ውስብስብ፣ ተለዋዋጭ እና ዘርፈ ብዙ ተግባር በመሆኑ በአንድ ተቋም ወይም ባለድርሻ አካላት ብቻ የሚቀረፍ ችግር ባለመሆኑ የሁሉንም የህብረተሰብ የነቃ ተሳትፎ እና ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል።

ድርጊቱ ተደራራቢና የተራዘመ ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ ሁሉም ዜጋ ከጥቃት ነፃ የሆነ ትውልድና ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለመገንባት የሚደረገው ጥረት ዘላቂና ውጤታማ እንዲሆን በቅንጅት መረባረብ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።

በፓናል ውይይቱ ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን እንደ ተቋም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ አካቶ ትግበራን በማጠናከርና ችግሩን ለመቅረፍ የሚያስችሉ መፍትሔዎችን መሻት እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ