+251118132191
contact@mint.gov.et
የ2025 የኢንተርኔት ልማት ኮንፈረንስ በአፍሪካ ኢጋድ አገሮች የኢንተርኔት የመሠረተ ልማት ተግዳሮቶችን ለመፍታትና አዳዲስ መፍትሄዎችን ለመተግበር የሚያስችል መሆኑን ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ገለፁ፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከበይነመረብ ማህበረሰብ (Internet Society) እና ከዊንጉ አፍሪካ (Wingu Africa) ጋር በመተባበር በአፍሪካ ኢጋድ አገሮች የኢንተርኔት ስነ-ምህዳር መሰረት ለመጣል የሚያስችል ለ3 ቀን ሲካሄድ የነበረው የኢንተርኔት ልማት ኮንፈረንስ ተጠናቋል።
የኮንፍረንሱ የመዝግያ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ በሀገራቱ መካከል የኢንተርኔት መለዋወጫ ነጥቦችን ተደራሽነትን ከማስፋፋት ጀምሮ የማህበረሰብ ኔትዎርክ ዕድገት ባልተሟሉ አካባቢዎች ሀብታችንን እና እውቀታችንን በመጠቀም አዳዲስ ውጤቶችን ማስመዝገብ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የአፍሪካ አህጉራዊ የነጻ ንግድ ስምምነትን (AfCFTA) ለመደገፍ አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከር አስፈላጊ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በአፍሪካ ኢጋድ አገሮች በጋራ ፖሊሲዎችንና ቴክኒካዊ ማዕቀፎችን ማውጣት ከድንበር በላይ በሆኑ የዲጂታል መሠረተ ልማት ላይ ኢንቨስትመንቶችን ለማሳደግ ያግዛል ብለዋል።
ኢጋድ አገሮች በጋራ እድል ድንበር የማይገድበው ፈጠራን እያንዳንዱን ማህበረሰብ የሚያንፀባርቅበት፣ ክልላችን በአለም አቀፍ ደረጃ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፋና ሆኖ የሚታይበትን እና የላቁ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም ወቅቱ የሚሻውና ወደ ተግባር መግባት አስገዳጅ እንደሆነ አስገንዝበዋል።
በዝግጅቱ መዝጊያ ላይ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ በኢጋድ አገሮች የዲጂታል ኢኮኖሚ ዕድገትን ከማፋጠን ባለፈ በአለም አቀፍ የዲጂታል ገበያ ግንባር ቀደም ተዋናይ ለመሆን መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡
በዘርፉ ድንበር ተሻጋሪ የእውቀት መጋራትን አቅም ለማጎልበት እና የመሠረተ ልማት ተግዳሮቶችን ለመፍታት ግኑኝነትንና ትብብርን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
በአዲስ አበባ ለ3 ቀን ሲካሄድ የነበረው በኢንተርኔት ልማት ኮንፈረንስ የተፈጠሩት ውይይቶች እና ስምምነቶች ስኬታማና ለተግባር የሚያነሳሱ እንደነበሩ ተገልፃል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች