+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

የ5 ሚሊዮን የኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ሰልጣኞች በቀጣይ የሀገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚ አቅም ናቸው።ዶ/ር በለጠ ሞላ

የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች ሀገራዊ የ2017 የመጀመሪያው የ100 ቀን እቅድ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ባመጣው ለውጥ ውስጥ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የነበረው ሚና ላይ መክረዋል።

የኢኖቬቨንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሀገራዊ ኢኮኖሚው ለማጎልበት የተወሰደውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ለውጥ በመጠቀም ከቴክኖሎጂ የሚጠበቀውን ውጤት በማስመዝገብ ዓለም የደረሰበት እድገት ላይ ለመድረስ ያለንን አቅም አሟጠን መጠቀም አለብን ብለዋል።

የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና የተቋሙ አንኳር ስራ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ የዲጂታል ኢኮኖሚያችን ግንባታ እንዲሳካ የኮደርስ ስልጠና በመሰልጠን ዜጎች የተሟላ የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው እንደሚያስችል አስገንዝበዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም የ5 ሚሊዮን የኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቭ ሰልጣኞች በቀጣይ የሀገሪቱ የዲጂታል ኢኮኖሚ አቅም ናቸው ብለዋል።

ሀገራዊ የ2017 የመጀመሪያው የ100 ቀን እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ሀገራችን በኢኮኖሚ እንድትበለፅግ ብዙ ሆነን እንደ አንድ ተናበን ከሰራን ያቀድናቸውን ወደ ውጤት መቀየር እንደሚቻል ገልፀዋል።

ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገታችን ፈጣንና እምርታዊ ለውጥ እንዲያመጣ አቅዶቻችን ተጨባጭ የሆኑ ውጤቶች ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው ብለዋል።

በቀረበው ሪፖርት ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ተገቢውን ምላሽ የሰጡ ሲሆን ሀገራዊ የልማት አፈፃፀሞችን ለተቋማትና ለሚመለከታቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ማቅረብ ወሳኝ ሚና እንዳለው ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

 

 

 

 

 

 

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ