+251118132191
contact@mint.gov.et
ያለንን ያልተነካ ፀጋ ወደ ሀብት ለመቀየር እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አንዱ የስታርትአፕ ስነምህዳር ማስፋትና ስራ ፈጠራን ማበረታት ነው። ዶ/ር ባይሳ በዳዳ
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በጃፓን አለማቀፍ ትብብር ኤጂንሲ (JICA) ውስጥ በሚገኘው ኒንጃ ዩኒቨርስቲ ስታርትአፕ ልማት ፕሮግራም እና R&D Group ጋር በመተባበር በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ ጀማሪ የስታርትአፕ ሀሳብ ያላቸው ተማሪዎች የንግድ ሀሳባቸውን ለማሳደግ እና የፈጠራ ስራዎቻቸውን ወደ ቢዝነስ እንዲቀይሩ ትልቅ ድጋፍ የሚያደርግ የስልጠናና ውድድር መርሀ ግብር አካሄደ።
ውድድሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ የተውጣጡ 23 ጅምር የስታርትአፕ ሀሳብ ያላቸው ተማሪዎች የተሳተፉበት ሲሆን ከነዚህ ከያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ የወጡት ተወዳዳሪዎች የእውቅናና ለስራቸው የሚያገለግላቸው የቁሳቁስ ሽልማት ተሰጥቷቸዋል።
በሽልማት ፕሮግራሙ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ መንግስት የጀመረውን በእውቀት የሚመራ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የኢኮኖሚ ጉዞ ውጤታማ ለማድረግ የስታርትአፕ እና የፈጠራ ስራዎች ትልቅ ድጋፍ ይኖራቸዋል ብለዋል።
እንደሀገር ያለንን ህልም እውን ለማድረግ መንግስት እየሰራቸው ያሉ ውጤታማ ስራዎች የስራ ሀብት ፈጠራ ስራዎች ትልቅ ድጋፍ ያደርጋሉ ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት ወጣቶች የፈጠራ ሀሳባቸው የሚያሳድጉበት እና ቴክኖሎጂን የማላመድና የመፍጠር አቅማቸው የሚያጎለብቱበት እድል እያመቻቸ ይገኛል ብለዋል።
በውድድሩ የ JICA ተወካይ ms. Sakiko korosaka መንግስት በዩኒቨርስቲዎች የሚደረገው የፈጠራ ሀሳብን የማጎልበት ሥልጠና እና ውድድር ወደሌሎች ዩኒቨርስቲዎች ለማስፋፋት የያዘውን እቅድ ለማሳካት የጃፓን መንግስት ድጋፍ ያደርጋል ብሏል።
ውድድሩ በአራት ዩኒቨርስቲዎች ማለትም በመቐለ፣ በጅማ፣ በአዲስ አበባ እና በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን በሚቀጥለው አመት በተለያዩ የኒቨርስቲዎች የሚተገበር ይሆናል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች