+251118132191
contact@mint.gov.et
ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በአካል የመገኘት ፍላጎትን እየቀነሱ ነው
ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት ለማግኘት በአካል የመገኘት ፍላጎትን እየቀነሱ መሆናቸው ገለጸ።
በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አማካሪ አብዮት ባዩ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ለዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት ጥሎ አልፏል ብለዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የዲጂታል ግብይቶችን፣ የፋይዳ መታወቂያ ስርዓትን፣ ኤሌክትሮኒክ መንግሥትን፣ ዲጂታል የቢዝነስ አካባቢን በማሻሻል ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱንም አመላክተዋል።
ከዚህ በመነሳት ተሞክሮዎችን በማጠናቀር የቀጣዩን ምዕራፍ ማለትም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ለማሳካት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብለዋል።
በጠንካራ የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣ በመንግስት ተቋማት መካከል የተቀናጁ ጥረቶች፣ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ እና በዓለም አቀፍ አጋርነት የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ቴክኖሎጂን ወደ ተለያዩ ዘርፎች ማሳደግ መቻሉን ገልጸዋል።
በዚህም በርካታ የመንግስት ተቋማት አገልግሎቶች ቀልጣፋ፣ ግልጽ እና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ አቅም መፈጠሩን የገለጹት አማካሪው፤ ይህም ለተለያዩ አገልግሎቶች በመንግስት መስሪያ ቤቶች በአካል የመገኘትን ፍላጎት በመቀነስ ጊዜንና ገንዘብን መቆጠብ አስችሏል ብለዋል።
ዲጂታል 2030 የሚፈለገውን ውጤት እንዲያስገኝ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ቀጣይነት ያለው ርብርብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 የዲጂታል መሠረተ ልማት እና የኢኮኖሚ ሽግግርን ለማፋጠን እንዲሁም ዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነች ኢትዮጵያን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑን ጠቁመዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች