+251118132191
contact@mint.gov.et
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ ክልሎች እና የከተማ መስተዳድሮች የማይተካ ሚናቸውን እየተወጡ መሆኑን ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ ገለፁ፡፡
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለክልሎች የዲጂታል ልማት አጋዥ እንዲሆኑ የተለያዩ ሲስተሞችን እና ዘመናዊ ዲጂታል የስብሰባ ማዕከላት (Smart Communication Room)በማስገንባት ላይ ይገኛል።
ከነዚህም ውስጥ የድሬዳዋ ከተማን አገልግሎት አሰጣጥ በኤሌክትሮኒክ አግባብ ለማሳለጥ እንዲያግዝ እያስለማው ያለውን የቢዝነስ ፖርታል እና እያስገነባ ያለውን ዘመናዊ ዲጂታል የስብሰባ ማዕከል (Smart Communication Room) የደረሱበትን ደረጃ ለመገምገም እና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ለመምከር የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሹሩን አለማየሁ በድሬዳዋ ከተማ ተገኝተው የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
መንግስት ሀገራዊ የዲጂታል ሽግግርን ለማምጣት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን በጉብኝቱ ወቅት ያወሱት ሚንስትር ዲኤታው የድሬዳዋ ከተማ የአገልግሎት አሰጣጥን በተለይም የግንባታ ፈቃድ እና የንብረት ምዝገባ አገልግሎቶችን በኤሌክትሮኒክ አግባብ ተደራሽ ለማድረግ የለማው ብሔራዊ የቢዝነስ ፖርታል ለዲጂታል ልማት ጉዞ አንድ ቁልፍ አስቻይ ነው ብለዋል።
ከተማዋ ካሏት የዲጂታል አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት እንደምትጠቀምበት ሙሉ እምነታቸው የገለጹት ሚንስትር ዴኤታው ቀጣይነቱን ለማረጋገጥም ከሚኒስቴር መስርያቤቱ በኩል ተገቢ ድጋፍ እንደሚደረግ አውስተዋል፡፡
ዘመናዊ ዲጂታል የስብሰባ ማዕከሉም ጊዜን እና ጉልበትን ከመቆጠብ ባሻገር በስብሰባዎች ለመታደም ይወጣ የነበረ ወጪን በማስቀረት ታዳሚዎች ካሉበት ሆነው እንዲሳተፉ የሚያስችል በመሆኑ ሀብትን ለመቆጠብ እና በፍጥነት መረጃዎችን በመለዋወጥ ስራን ለማሳለጥ እንደሚያግዝ ሚንስትር ዴኤታው ጠቁመዋል፡፡
በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ድጋፍ መሰል ፕሮጀክቶች በሌሎች ክልሎችም እየተገነቡ መሆኑን የጠቀሱት ዶ/ር ይሹሩን በአጠቃላይ ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ ክልሎች እና ከተማ መስተዳድሮች የማይተካ ሚናቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልፀው ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ጥረታቸውን አጠናክረው እንዲያስቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የድሬደዋ ከተማዋ ከንቲባ አቶ ከድር ጁሀር በበኩላቸው በሚኒስቴር መስሪያቤቱ በኩል እየተደረገ ያለውን ድጋፍ በማድነቅ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን ከተማዋ ነፃ የንግድ ቀጠና (Free Trade Zone) የሚገኝባት እንደመሆኗ መጠን ቀጠናው የሚፈልገውን የዲጂታል ልማት ለማረጋገጥ እና በአጠቃላይም ለሀገራዊ የዲጂታል ልማት ጉዞ የከተማ መስተዳድሩ የበኩሉን አበርክቶ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት ለከተማ አስተዳደሩ የግንባታ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን አነስተኛ ማሰልጠኛ ማዕከል ማቋቋሚያ የሚሆኑ የላብቶፖች፣ የዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች እና የፌርኒቸሮ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች