+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 መቶ በመቶ የተሳካ እቅድ ነው።አሁን ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እየተዘጋጀ ይገኛል።ይህም በሀገራችን እውቀት መር ኢኮኖሚ ለመገንባት መሰረት ይጥላል።ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከ“ቴክ ቶክ ሰለሞን ጋር” በክፍል አንድ በነበራቸው ቆይታ የሰው ሠራሽ አስተውሎት(አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ - ኤ አይ) በዲጂታል እኮኖሚና በሌሎችም የቴክኖሎጂ ዘርፎች በርካታ ጉዳዮች አንስተዋል።ከነዚህ መካከል

👉 በሀገራችን ቴክኖሎጂ በሲቪል ሰርቪስ፣ በሕግ ማስከበር፣ በመከላከያ፣ በሚዲያ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ ዘርፎች ያሉ ሥራዎችን ለማሳካት እና ለማሳለጥ ጥቅም ላይ እዋለ ነው፡፡

👉 ዕውቀት ችግር እስካልፈታ ድረስ በዕውቀት መስፈርት ውስጥ ሊታይ የሚያስችል ብቃት አይኖረውም።

👉 በኢትዮጵያ እስከ ቀጣይ ዓመት ድረስ በአጠቃላይ ወደ 55 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ ነው፤ ይህም ይህም በዓለም ላይ ትልቁ የደን ማልማት ሥራ ይሆናል፡፡

👉 ከሌሎች ሴክተሮች ዕቅድ አንጻር ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ሙሉ በሙሉ ተሳክቷል፡፡ አሁን ላይ ለዲጂታል 2030 ዝግጅት እየተደገ ነው፡፡

👉 በሀገራችን ቴክኖሎጂ በሲቪል ሰርቪስ፣ በሕግ ማስከበር፣ በመከላከያ፣ በሚዲያ፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ ዘርፎች ያሉ ሥራዎችን ለማሳካት እና ለማሳለጥ ጥቅም ላይ እዋለ ነው፡፡

👉 የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመት ከ100 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን ማጓጓዝ የሚያስችል ዕቅድ እና ለዚህም የሚያግዘውን አዲስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እየሠራ ነው፡፡

👉 በመከላከያ ሠራዊት ውስጥ ሎጂስቲክስ የሚያጓጉዙ ድሮኖች እንዲሁም በሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤ አይ) የሚንቀሳቀሱ ተዋጊ ጀቶች ጥቅም ላይ እየዋሉ ይገኛሉ።

👉 ከዓመታት በፊት የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት በአፍሪካ በጣም ውድ ነበር፤ አሁን ላይ ግን በአህጉሪቱ በዝቅተኛ ዋጋ አገልግሎቱን ማቅረብ ተችሏል፡፡

👉 በአሁኑ ወቅት 51 ሚሊየን ገደማ ሰዎች የሞባይል ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

👉 የሰው ሠራሽ አስተውሎት(አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ - ኤ አይ) አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በፒኤችዲ ደረጃ መሰጠት ተጀምሯል።

👉 በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከ“ቻት ጂፒቲ” ወይንም “ዲፕ ሲክ” ጋር ተመሳሳይነት ያለው “መላ” የተሰኘ የሀገር ውስጥ ቋንቋን በስፋት የሚጠቀም የኤአይ ሥርዓት ተገንብቷል፡፡

👉 የአፍሪካ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) ሰሚት በአዲስ አበባ ከተማ ይካሄዳል። በዚሁ ወቅት 1 ሺህ ገደማ ድሮኖች በኤአይ ታግዘው ትርዒት ያቀርባሉ፡፡

👉 የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በአፍሪካ ውስጥ ቀዳሚ ሚና አለው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮም ሁሉ የአፍሪካውያን ኩራት መሆን ይችላል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ