+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬታማ ለማድረግ ድንበር የለሽ የዲጂታል ኢኮኖሚን ግንባታ ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ይሽሩን አለማየሁ ገለፁ፡፡

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስኬታማ ለማድረግ ድንበር የለሽ የዲጂታል ኢኮኖሚን ግንባታ ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ / ይሽሩን አለማየሁ ገለፁ፡፡

============

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ የዲጂታል ገበያ ትስስር ፕሮጄክት አስተዳደር አባላት ጋር በዲጂታል ክፍያ፣ ዳታ ሴንተር፣ በበይነ-መረብ ደህንነትና የኤሌትሮኒክ ማረጋገጫ ማዕከል እና በኤሌክትሮኒክ ዌስት አስተዳደር ማዕከል ግንባታ በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና ሶማሊያ ላይ ለመገንባት የአዋጪነት ጥናት ሰነድ ለማዘጋጀት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ / ይሽሩን አለማየሁ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዟችንን በማሳለጥ ከሌሎች አጋር ሀገሮች እና ቀጠናዊ ተቋማት ጋር ትብብርና ትስስር በመፍጠር ለሀገራዊ እና አህጉራዊ ኢኮኖሚ ብልፅግና ግስጋሴ አስተዋፆ የሚያደርግበት ስርዓት መፈጠር እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታውን ለማፋጠን ኢትዮጵያ ድንበር የለሽ የዲጂታል ገበያ ትስስር ለመፍጠር በምታደርጋቸው ጥረቶች ውስጥ በተለይ ከአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ጋር ቅድሚያ ሰጥታ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት በትብብር ትሰራለች ብለዋል፡፡

ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ የዲጂታል ገበያ ትስስር ፕሮጀክት አስተዳደር አባላት አስተባባሪ አቶ ዳንኤል ሙቱሪ የፕሮጀክቱን አዋጭነት ጥናት ለማከናወን የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ፕሮጀክቱን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር በመስራት የሚፈለገውን ውጤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማምጣት እንሰራለን ብለዋል፡፡

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በተደረገው የአፍሪካ ቀንድ የድጂታል ገበያ ትስስር መድረክ ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንና፣የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና ኢትስዊች ተሳትፈውበታል፡፡

ከምስራቅ አፍሪካ በይነ መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ቀንድ የዲጂታል ገበያ ትስስር ፕሮጄክት አባል ሀገራቱን ማዕከል ያደረገ አንድ የዲጂታል ገበያ ትስስር ለመፍጠር ያለመ ስራን እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡፡

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ