+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለማሳካት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ሪፎርም እጅግ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ2018 በጀት አመት የስድስት ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሪፎርምና በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስራቴጂና የስታርታፕ የተግባር እቅድ ላይ መክረዋል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የኢትዮጵያን የወደፊት ታላቅነት የሚያረጋግጠውን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለስኬት የሚያበቁ እቀዶችን አቅደን ልንሰራ ይገባል ብለዋል።

ሪፎርም እንደለውጥና የስኬቶች ሁሉ መሰረት ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው በለውጥ ውስጥ ያለችው ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያስቸላትን አቅም በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚዋን እየገነባች መሆኗን አንስተዋል።

ከዲጂታል አለም ጋር ተግባብቶ በመስራት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስኬትን ማረጋገጥ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚው አውድ የሚጠይቀው ግዴታ ጭምር መሆንኑ በመግለፅ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ መዝጊያ ፕሮግራም ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቴክኖሎጂ ዘርፉ ተወዳዳሪ ለማድረግ አለም የታጠቀውን ክህሎት ባለቤት እንድትሆን ፈጣን ሁለንተናዊ ተግባር እየተከናወነ መሆኑን ገልፀዋል።

ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የሁሉም መሰረት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የኢትዮጵያ ስታርታፕ ዲጂታል ፕላትፎርም ዘርፉን ለማሳደግ እና ኢኮኖሚውን የመደገፍ ፋይዳ አለው ብለዋል።

አክለውም የስታርታፕ አዋጅ በተገቢው መንገድ ተግባራዊ ማድረግ በሀገራዊ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ሚ፣ና ስላለው ሁሉም የዘርፉ ተዋናይ ህሳቤውን በመረዳት ወደ ተግባር የመቀየር ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በመጨረሻም የታቀዱ እቅዶችን በመከለስ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተዋናዮች የሰው ሀይል ግንባታ ላይ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ