+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ዶ/ር በለጠ ሞላ ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሁሴን ጋር ተወያዩ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በአሶሳ ከተማ ተገኝተው ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሌ ሁሴን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ውይይቱ በክልሉ አሶሳ ከተማ የወጣቶችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማሳደግና የስታርታአፕ ስነምህዳር ለማነቃቃት የሚያግዝ የሳይንስ ካፌ ማዕከልን የሪኖቬሽንና ማደራጀት ስራዎችን ለማከናውን በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው።

በውይይቱ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በክልሎች የቴክኖሎጂ ተጠቃማነትን ለማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በማከናወን ላይ እንደሚገኝ በመግለጽ በተለይም የወጣቶችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ባለፉት አመታት በተለያዩ ክልሎች የሳይንስ ካፌዎችን በመገንባት ለአገልግሎት ማዋሉን አስታውሰዋል።

ክቡር ሚኒስትሩ አያይዘውም የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ወጣቶችም ከስታርታፕ ስነምህዳር ግንባታ አኳያ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለክልሉ እድሉን እንዳዘጋጅ ጠቅሰው ማዕከሉን ሪኖቬሽንና ማደራጀት ስራዎችን ለማከናወን በክልሉ በኩል አስፈላጊው ሁኔታ ተመቻችቶ ስራው በአስቸኳይ መጠናቀቅ እንደሚገባው ገልጸዋል።

በተደረገው ውይይት በክልሉ በኩል አሰፈላጊውን ሁኔታ የማመቻቸት ስራ በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃል ያሉት የክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አሻድሌ ሁሴን ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ለክልል ያስገነባው የስማርት ኮሙኒኬሽን ክፍል በክልሉ ለሚከናወኑ ስራዎች መቀላጠፍ የሚኖረው ፋይዳ የጎላ እንደሚሆን ጠቅሰው ለዚህ ተግባር ሚኒስቴር መስርያቤቱን አመስግነዋል።

ክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ አያይዘውም ክልል ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መገኛ እንደመሆኑ መጠን

በግድቡ የተፈጠረውን ከፍተኛ የአሳ ሃብት ልማት ስራ ለማገዝና የሚገኘውን ምርት ጥራት በመጠበቅ ለገበያ ለማቅረብ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ስራውን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ እንዲያግዘው ጠይቀዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ በሁሉም የክልል ዋና ከተሞች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በተመረጡ የፌደራል ተቋማት ካስገነባቸውን 24 የስማርት የኮሚኒኬሽን ክፍሎች ውስጥ አንዱ በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ከተማ መመረቁ ይታወሳል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ