+251118132191

contact@mint.gov.et

Font Awesome Icons
Fixed Header Menu Example

ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ የማህበረሰቦች ዕውቀት፣ ባህልና ዕሴቶች የሥልጣኔ ምሶሶዎች ናቸው፡፡ዶ/ር ባይሳ በዳዳ

በአለም አእምሯዊ ንብረት ድርጅት (WIPO) እና በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ትብብር እንዲሁም በጃፓን ፓተንት ጽ/ቤት (JPO) አጋርነት ሲካሄድ የቆየው ብሄራዊ የአእምሯዊ ንብረት ሳምንት ተጠናቋል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ድኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የአእምሯዊ ንብረት ሳምንቱ የአእምሯዊ ንብረት ስርዓት ዓለም አቀፋዊ ይዘት፣ ልምድ፣ የህግ ማዕቀፍ እና ተግባራዊነትን በማሳየት የሃገራችንን የአእምሯዊ ንብረት ሥርዓት ለማሻሻል የጋራ ግንዛቤ እንዲኖረን አስተዋጽዖው የጎላ ነው ብለዋል።

ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፣ የማህበረሰቦች ዕውቀት፣ ባህልና ዕሴቶች የሥልጣኔ ምሶሶዎች ናቸው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው መንግስት ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ሚንስትር ድኤታው አያይዘውም ሃገራችን በጀመረችው ዘላቂ የልማት ግቦችን የማሳካት ጉዞ እየተተገበረ ባለው ሃገር በቀል /Home grown/ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ዘመኑ በሚጠይቀው የቴክኖሎጂ አቅምና ዲጂታል ስርዓት መደገፍ ያስፈልጋል ብለዋል።

በለፉት የለውጥ አመታት አስፈላጊ የሆኑ የስነምህዳር ግንባታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ያነሱት ሚኒስትር ድኤታው የመሠረተ ልማት ግንባታ ስራዎች፣ ነገን ታሳቢ ያደረጉ ሀብት፣ ፈጣራና የሰው ሀብት ልማት ስራዎች የዘርፉን አፈጻጸም ከማሳደግ አንጻር ጉልህ ሚና እንደሚኖራቸው አንስተዋል።

የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመሰል ላለፉት አምስት ቀናት ሲካሄድ የነበረው ብሄራዊ የአእምሯዊ ንብረት ሳምንት ሦስት ብሄራዊ ወርክሾፖች የተካሄዱበት መሆኑን ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ዩኒቨርስቲዎችና የምርምር ተቋማት ያለው ፋይዳ እንዲሁም የህግ አውጪዎችና አስፈጻሚዎች ግንዛቤና ድጋፍ አስፈላጊነት የዳሰሱ ወርክፖሾፖች ውጤታማ እንደነበሩም ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

በብዛት የተጎበኙ

News Card Example

መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ     በ2011 ዓ.ም  የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር  ተቋቋመ፡፡

የትኩረት መስኮች

  • ምርምር
  • ኢኖቬሽን
  • የቴክኖሎጂ ሽግግር
  • ዲጂታላይዜሽን

ያግኙን

  • ስልክ: +251118132191
  • ኢሜል: contact@mint.gov.et
  • ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et

የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች

Font Awesome Icons

©2024 MINT መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ከእርምጃ ወደ ሩጫ