+251118132191
contact@mint.gov.et
“ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂ በመተግበር የተመዘገቡ ውጤቶችን አስተማማኝ ለማድረግ የቴክኖሎጂ ተቋማት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ፡፡
በፌዴራል የዘርፍ ሚኒስቴር ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ያተኮረው የምክክርና የግምገማ መድረክ በትናንትናው ዕለት የመሰረተ ልማት ዘርፍ አፈፃፀምን በመገምገም የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በምክክር መድረኩ “ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025” ስትራቴጂ በዋናነት የዲጂታል መሰረተ ልማት በመገንባትና በማስፋት የአገሪቱን ምጣኔ ኃብታዊ እድገት ማፋጠንን ዓላማ ባደረገው እንቅስቃሴ በበጀት ዓመቱ በግብ የተቀመጡ ልዩ ልዩ ተግባራት ውጤቶች መመዘግባቸውን ገምግሟል፡፡
በዚሁ መሰረት የተመዘገቡ ውጤቶች አስተማማኝ ለማድረግ እንዲቻል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት፤ የኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን፣ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት እና የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው ተገልጿል፡፡
የቴክኖሎጂ ተቋማቱ የምርምርና ልማት ስራዎች ውጤታማነትን የማረጋገጥ፤ የገቢ ምንጭን አማራጮችን የማስፋት፤ ልዩ ልዩ የበለፀጉ ሶፍትዌሮችን የባለቤትንትንና ዘላቂ ጠቀሜታ እንዲኖራው የማስቻል፤ የቴክኖሎጂ ዘርፉ በሀገራዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ ላይ ድርሻ እንዲኖረው በማድረግና በሌሎች የተለያዩ ተግባራት ላይ ተናበውና ተቀናጅተው በመስራት የተጣለባቸውን አደራ ማከናወን እንዳለባቸው ተጠቁሟል፡፡
የፕላንና ልማት ሚኒስቴር የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ዝግጅትን በገመገመበት ወቅት የበጀት አመቱ የዘርፍ እቅድ አፈፃፀም እና ያሉ ሀገራዊ ለውጦችን እንዲሁም ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የገመገመ ሲሆን በቀጣይ ሁሉንም ዜጋ ተደራሽ በማድረግና ግልፅ እና ወቅታዊ ሁኔታን መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የመረጃ ስርአቱ መዘርጋት እንደሚገባ ጭምር ተገልጿል።
የምክክርና ግምገማ መድረኩ ሶስተኛ ቀን ውሉ በነዚህ ጉዳዬች የተወያየ ሲሆን መድረኩ እስከ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ እንደሚቀጥል የወጣው መርሐ ግብር ያመለክታል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች