+251118132191
contact@mint.gov.et
22ኛው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት 22ኛውን የፀረ ሙስና ቀን ‘’ትውልድን በስነ-ምግባር፣ ተቋምን በአሰራር’’ በሚል መሪ ቃል በመስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አከበሩ፡፡
በመድረኩ የመክፈቻ ንግግሩ ያደረጉት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ሙስና ባህሪያዊና ድርጊታዊ መሆኑን በመግለጽ በተለይ ሁሌም እራሳችንን የተሻለ እውቀትና ግንዛቤ ላይ በማዋል ካላስፈላጊ ድርጊቶች ልንጠብቅ ይገባል ብለዋል፡፡
ሚኒስትሩ አያይዘውም ተቋማት ሁለንተናዊ ስራዎቻቸው ላይ አድሎዊ ያሰራር ስርዓትን፣ በስራ ቦታ በሰዓት አለመገኘትን፣ የማይገባ ጥቅምን ለማግኘት የሚደረጉ ጥረቶች ሁሉ ሙስና መሆናቸውን ተረድቶ ካላስፈላጊ ድርጊቶች መጠበቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከተሰጡት ኃላፊነቶች ቁልፉ በሆነው ተግባር ተቋማትና የስራ ሂደቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማዘመንና በመደገፍ የአሰራር ስርዓቶችን በመፍጠርና ግልፀኝነትን በማንገስ ሙስናን መቀነስ የሚቻልበት ስርዓት እየተፈጠረ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
የፌደራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ክቡር አቶ ፍቃዱ ሰቦቃ የዘንድሮ የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በስነምግባር፣ ተቋማትን በአሰራር” በሚል መሪ ቃል ስናከብር ትውልዱ የሙስናና ብልሹ አሰራር የሀገር ውድቀት መሆኑን በማስገንዘብና የተቋማትን አሰራር በማዘመን ውጤታማነትን ማረጋገጥ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ በፌዴራል ስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን የተዘጋጀ በተቋማት አሰራርና ሙስና መከላከል ላይ ያተኮረ የድምፅ መልዕክት ሰነድ ቀርቦ ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡
በመጨረሻም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የሀብት ምዝገባ ሰነድን ለፌዴራል የሥነምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን አስረክበዋል።
በብዛት የተጎበኙ
መንግስት የቀድሞው የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በማዋሃድ በ2011 ዓ.ም የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተቋቋመ፡፡
የትኩረት መስኮች
- ምርምር
- ኢኖቬሽን
- የቴክኖሎጂ ሽግግር
- ዲጂታላይዜሽን
ያግኙን
- ስልክ: +251118132191
- ኢሜል: contact@mint.gov.et
- ድረ-ገጽ: www.mint.gov.et
የማህበራዊ ሚዲያ ትስስር ገጾች